የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ ለነቢዩ ዘካርያስ በርካታ አስደናቂ ራእዮችን አሳይቶታል። ዘካርያስ ያያቸው ራእዮች እሱም ሆነ የይሖዋ ሕዝቦች ንጹሑን አምልኮ መልሰው ለማቋቋም ጥረት ሲያደርጉ ያጋጠሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ለመወጣት ረድተዋቸዋል። እነዚህ ራእዮች እኛም ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩብንም ይሖዋን በታማኝነት ማገልገል እንድንችል ይረዱናል። በዚህ ርዕስ ውስጥ፣ ዘካርያስ ካያቸው ራእዮች መካከል ከአንዱ የምናገኘውን ጠቃሚ ትምህርት እንመለከታለን፤ ራእዩ ስለ መቅረዝና የወይራ ዛፎች የሚገልጽ ነው።