የግርጌ ማስታወሻ
a አፍቃሪና አሳቢ የሆኑ ሽማግሌዎች እኛን ለመርዳት ሲሉ በትጋት ለሚያከናውኑት ሥራ በጣም አመስጋኞች ነን! በዚህ ርዕስ ውስጥ ሽማግሌዎች ብዙ ጊዜ የሚያጋጥሟቸውን አራት ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንመለከታለን። በተጨማሪም የሐዋርያው ጳውሎስ ምሳሌ በዛሬው ጊዜ ያሉ ሽማግሌዎች እነዚህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዲያሸንፉ የሚረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን። ይህ ርዕስ ሁላችንም የሽማግሌዎችን ስሜት እንድንረዳ ያግዘናል፤ እንዲሁም ፍቅር እንድናሳያቸውና እንድንደግፋቸው ያነሳሳናል።