የግርጌ ማስታወሻ
a ጢሞቴዎስ ብቃት ያለው የምሥራቹ ሰባኪ ነበር። ሆኖም ሐዋርያው ጳውሎስ መንፈሳዊ እድገት ማድረጉን እንዲቀጥል አበረታቶታል። ጢሞቴዎስ የጳውሎስን ምክር ከተከተለ ይሖዋን እንዲሁም ወንድሞቹንና እህቶቹን ይበልጥ ማገልገል ይችላል። አንተስ እንደ ጢሞቴዎስ ይሖዋንና የእምነት ባልንጀሮችህን ይበልጥ ለማገልገል ትጓጓለህ? እንደምትጓጓ ጥያቄ የለውም። ታዲያ እንዲህ ለማድረግ የሚረዱህ የትኞቹ ግቦች ናቸው? እነዚህን ግቦች ማውጣትና ግቦችህ ላይ መድረስ የምትችለውስ እንዴት ነው?