የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር ለማለት ይጓጓል። እኛ ክርስቲያኖችም አንድ ሰው ሲበድለን የይሖዋን ምሳሌ መከተል አለብን። እኛ በራሳችን ይቅር ብለን ልናልፍ ስለምንችላቸው ኃጢአቶች እንዲሁም ለሽማግሌዎች መናገር ስላለብን ኃጢአቶች በዚህ ርዕስ ውስጥ እንመለከታለን። ይሖዋ እርስ በርስ ይቅር እንድንባባል የሚፈልገው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ሌሎችን ይቅር ስንል ምን በረከቶችን እንደምናገኝም እንመለከታለን።