የግርጌ ማስታወሻ
b ተጨማሪ ማብራሪያ፦ “መንፈሳዊ ገነት” ይሖዋን በአንድነት የምናመልክበትን ደህንነቱ የተጠበቀ ሁኔታ ያመለክታል። በዚህ መንፈሳዊ ገነት ውስጥ ከሃይማኖታዊ ውሸቶች የጸዳ የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ እናገኛለን። እንዲሁም የአምላክን መንግሥት ምሥራች የመስበክ አርኪ ሥራ አለን። ከይሖዋ ጋር የቀረበ ዝምድና አለን። እንዲሁም አፍቃሪ ከሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በሰላም እንኖራለን፤ እነሱም በሕይወታችን ውስጥ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን በደስታ ለመጽናት ይረዱናል። ወደዚህ መንፈሳዊ ገነት የምንገባው ይሖዋን በትክክለኛው መንገድ ማምለክ ስንጀምርና እሱን ለመምሰል የቻልነውን ሁሉ ጥረት ስናደርግ ነው።