የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ ከባቢሎን ወደ እስራኤል የሚወስደውን ምሳሌያዊ አውራ ጎዳና “የቅድስና ጎዳና” በማለት ጠርቶታል። በዘመናችንስ ይሖዋ ለሕዝቦቹ መንገድ አዘጋጅቶላቸዋል? አዎ! ከ1919 ዓ.ም. አንስቶ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከታላቂቱ ባቢሎን ወጥተው ‘በቅድስና ጎዳና’ ላይ መጓዝ ጀምረዋል። ሁላችንም ወደ መዳረሻችን እስክንደርስ ድረስ በዚህ ጎዳና ላይ መጓዛችንን መቀጠል ይኖርብናል።