የግርጌ ማስታወሻ b ልክን ማወቅና ትሕትና ተቀራራቢ ባሕርያት ናቸው። ለራሳችንና ላለብን የአቅም ገደብ ተገቢውን አመለካከት በመያዝ ልካችንን እንደምናውቅ እናሳያለን። ራሳችንን ከሌሎች ዝቅ አድርገን በመመልከት ደግሞ ትሑት መሆናችንን እናሳያለን። (ፊልጵ. 2:3) በጥቅሉ ሲታይ፣ ልኩን የሚያውቅ ሰው ትሑት መሆኑ አይቀርም።