የግርጌ ማስታወሻ a ይሖዋ ከክርስትና ዘመን በፊት የነበሩትን አገልጋዮቹን ገና ቤዛው ባይከፈልም እንኳ ኃጢአታቸውን ይቅር ብሎላቸዋል። ይሖዋ ይህን ያደረገው ልጁ እስከ ሞት ድረስ ታማኝነቱን እንደሚጠብቅ እርግጠኛ ስለነበረ ነው። በመሆኑም በአምላክ ዓይን ያኔም ቤዛው እንደተከፈለ ሊቆጠር ይችላል።—ሮም 3:25