የግርጌ ማስታወሻ a ጴጥሮስ ጥልቅ ስሜቶች ያሉት ሰው ስለነበር ኢየሱስ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ምን እንደተሰማውና ምን እንዳደረገ ለማርቆስ ሕያው አድርጎ ሊገልጽለት ይችላል። ማርቆስ በወንጌል ዘገባው ውስጥ ስለ ኢየሱስ ስሜትና ድርጊት አዘውትሮ የጠቀሰው ለዚህ ሊሆን ይችላል።—ማር. 3:5፤ 7:34፤ 8:12