የግርጌ ማስታወሻ
b ለምሳሌ ያህል፣ በ785 ዓ.ም. ገደማ ሻርለማኝ ለመጠመቅና ክርስቲያን ለመሆን ፈቃደኛ ባልሆኑ በሳክሶኒ በሚገኙ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት የሚበይን አዋጅ አውጥቶ ነበር። በተጨማሪም በ1555 ዓ.ም. በቅዱሷ የሮማ ግዛት በሚገኙ የጦር አንጃዎች መካከል የተፈረመው የኦግስበርግ የሰላም ስምምነት አገረ ገዢዎች የሮማ ካቶሊክ ወይም የሉተራን አማኝ እንዲሆኑ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው የገዢውን ሃይማኖት እንዲከተል የሚደነግግ ሕግ ነበረው። የገዢዎቻቸውን ሃይማኖት ለመከተል ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ይደረግ ነበር።