የግርጌ ማስታወሻ
a ‘ነፍስ አትሞትም’ የሚለው ትምህርት እና የሪኢንካርኔሽን እምነት የተጀመረው በጥንቷ ባቢሎን ነበር። በኋላ ደግሞ የሕንድ ፈላስፎች የካርማን መሠረተ ትምህርት አመጡ። ብሪታኒካ ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ዎርልድ ሪሊጅንስ እንደሚናገረው ካርማ “በድርጊት እና በውጤት ሕግ” ላይ የተመሠረተ ነው። “በዚህ ሕግ መሠረት አንድ ሰው በአሁኑ ሕይወቱ የሚያደርገው ነገር ዳግመኛ ሲወለድ በሚኖረው ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።”—ገጽ 913