የግርጌ ማስታወሻ
a የጥንት አይሁዶች “ዘፀ[አት] 20 ቁጥር 2ን የመጀመሪያው ‘ቃል’፣ ከቁጥር 3-6 ያሉትን ደግሞ በአንድነት እንደ ሁለተኛ” አድርገው ይቆጥሯቸው ነበር። (ዘ ጂዊሽ ኢንሳይክሎፒድያ) በሌላ በኩል ግን ካቶሊኮች ዘፀአት ምዕራፍ 20 ከቁጥር 1-6 እንደ አንድ ትእዛዝ ሊቆጠር እንደሚገባ ይናገራሉ። በዚህ መሠረት፣ የአምላክን ስም በከንቱ ማንሳት ተገቢ እንዳልሆነ የሚገልጸው ትእዛዝ ሁለተኛ ትእዛዝ ይሆናል። ካቶሊኮች አጠቃላይ የትእዛዛቱ ቁጥር አሥር እንዲሆን ለማድረግ፣ የባልንጀራን ሚስትና ንብረት መመኘት ተገቢ እንዳልሆነ የሚገልጸውን ትእዛዝ እንደ ሁለት ትእዛዝ አድርገው ይቆጥሩታል።