የግርጌ ማስታወሻ a ይህ መዝሙር በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ የሚገኘው መዝሙር 22 ላይ ነው። በአጠቃላይ 150 መዝሙሮች ቢኖሩም አንዳንድ ትርጉሞች የመዝሙሮቹን ቁጥር የመደቡት በዕብራይስጡ የማሶሬቶች ጽሑፍ መሠረት ሲሆን ሌሎች ትርጉሞች ደግሞ የግሪክኛውን ሰብዓ ሊቃናት አቆጣጠር ተከትለዋል፤ ሰብዓ ሊቃናት በሁለተኛው ዓ.ዓ. የተጠናቀቀ የዕብራይስጡ ጽሑፍ ትርጉም ነው።