የግርጌ ማስታወሻ
a ከJW ላይብረሪ ላይ አንድ ነገር ሲወርድ የሚጠይቀው አነስተኛ ወጪ አለ። ለምሳሌ ያህል ባለፈው ዓመት ከjw.org እና ከJW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ላይ ቪዲዮዎችን በቀጥታ ለሚያጫውቱ እንዲሁም የተለያዩ ነገሮችን ለሚያወርዱ ተጠቃሚዎቻችን አገልግሎት ለመስጠት ስንል ከ1.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ አድርገናል። እንደዚያም ሆኖ ይህ ወጪ የታተሙ ጽሑፎችን፣ ሲዲዎችን እና ዲቪዲዎችን ማዘጋጀትና ከቦታ ቦታ ማጓጓዝ ከሚጠይቀው ወጪ በጣም ያነሰ ነው።