የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g01 5/8 ገጽ 32
  • ‘ትምህርታዊና እውቀት ሰጪ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ትምህርታዊና እውቀት ሰጪ’
  • ንቁ!—2001
ንቁ!—2001
g01 5/8 ገጽ 32

‘ትምህርታዊና እውቀት ሰጪ’

ንቁ! መጽሔትን አስመልክቶ ከላይ ያለውን የተናገረው በፓፕዋ ኒው ጊኒ ደጋማ ክልል የሚኖር የ26 ዓመት ሰው ነው።

ይህ ሰው በዚያ ለሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ደብዳቤ በመጻፍ “ተወዳጅ በሆነው ንቁ! መጽሔታችሁ ላይ የሚደነቁ፣ በሐቅ ላይ የተመሠረቱ፣ ትምህርታዊና እውቀት ሰጪ ርዕሶችን ስለምታወጡ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” ብሏል። ሰውዬው “ምንም እንኳ እኔ የይሖዋ ምሥክሮች እምነት አባል ባልሆንም ከጓደኞቼ የምዋሳቸውን ንቁ! መጽሔቶች ከዳር እስከ ዳር አነብባቸዋለሁ። . . . እያንዳንዱን መጽሔት አንብቤ በጨረስኩ ቁጥር ላደረጋችሁት ትጋት የታከለበት ጥረት በደብዳቤ ላመሰግናችሁ አስባለሁ። ሆኖም ለመጻፍ ስነሳ ሌላ መጽሔት ይደርሰኝና እንደገና ጊዜ አጣለሁ።”

አድናቂ የሆነው ይህ አንባቢ “በእኔ አመለካከት ንቁ! መጽሔት ማንበብ ለሚችል ለማንኛውም ሰው በእርግጥ ጠቃሚ ነው። ከልብ ነው የምላችሁ ምስጋናዬ ወደር የለውም” በማለት ደምድሟል።

ንቁ! የተለያዩ ርዕሶች ይዞ ስለሚወጣ እውቀት ይገኝበታል። ከሁሉም በላይ አሁን ያለውን የነገሮች ሥርዓት የሚተካ ሰላም የሰፈነበት አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ፈጣሪ በሰጠው ተስፋ ላይ ሰዎች ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ ያደርጋል።

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ለማሳየት ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህን የአምላክን ዓላማ የሚያጎላ ትምህርት ያቀርባል። እርስዎም የዚህን ብሮሹር አንድ ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ።

□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ