የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g02 7/8 ገጽ 32
  • “ባሳየው ፍቅር ተማርኬአለሁ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ባሳየው ፍቅር ተማርኬአለሁ”
  • ንቁ!—2002
ንቁ!—2002
g02 7/8 ገጽ 32

“ባሳየው ፍቅር ተማርኬአለሁ”

በኒስ ከተማ የሚኖር አንድ ሰው ዩጎዝላቪያ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በላከው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብሏል:-

“በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በየዕለቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰኑ ምዕራፎች አነብባለሁ። እንዲህ ማድረጌ ያስደስተኛል። ሰሞኑን ደግሞ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አንብቤአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚያስችል እንዲህ ዓይነት ግሩም ጽሑፍ ስላዘጋጃችሁ አመሰግናችኋለሁ። ብሮሹሩ በጣም ግልጽና ለመረዳት ቀላል በሆነ መንገድ የተዘጋጀ ነው።

“በተለይ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገረው ትምህርት በጣም አስደስቶኛል። ለማያውቃቸው ሰዎች ሳይቀር ፍጹም ሕይወቱን በመስጠት ባሳየው ፍቅር ተማርኬአለሁ። ሰው ሁሉ ስለዚህ የኢየሱስ መሥዋዕት በቂ ግንዛቤ ሊኖረውና አመስጋኝ ሊሆን ይገባል።”

እርስዎም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ቢያነቡ እንደሚጠቀሙ እናምናለን። “ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?” ከሚለው ማራኪ ርዕሰ ትምህርት በተጨማሪ “እውነተኛው አምላክ ማን ነው?”፣ “አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?” እና “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?” እንደሚሉት ያሉ ሌሎች ትምህርቶችንም ያገኙበታል። እርስዎም አንድ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ።

□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ