የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g03 2/8 ገጽ 32
  • ነፋስ አምጥቶ የጣለው በራሪ ወረቀት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ነፋስ አምጥቶ የጣለው በራሪ ወረቀት
  • ንቁ!—2003
ንቁ!—2003
g03 2/8 ገጽ 32

ነፋስ አምጥቶ የጣለው በራሪ ወረቀት

በሕንድ ሙምባይ ከተማ ውስጥ አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲሄድ ኃይለኛ ነፋስ አንድ በራሪ ወረቀት አምጥቶ እግሩ ሥር ጣለው። በራሪ ወረቀቱ “አዲሱ ሺህ ዓመት​—⁠የወደፊቱ ጊዜ ምን ተስፋ ይዞልሃል?” የሚል ርዕስ ያለው የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ነበር። ርዕሱ ትኩረቱን ስለሳበው ፈጠን ብሎ ከመሬት አነሳውና ከዳር እስከ ዳር አነበበው። ያነበበው ነገር ፍላጎቱን ስለቀሰቀሰበት ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጽሑፎች እንዲላኩለት ጠየቀ።

በይሖዋ ምሥክሮች የታተመው ይህ በራሪ ወረቀት እምነት የሚያጠናክሩ ሐሳቦችን ይዟል። በዛሬው ጊዜ ያሉት እንደ ሕመም፣ ድህነትና ጦርነት ያሉ ችግሮች መንስዔያቸው በሳይንሳዊ ምርምር፣ በቴክኖሎጂ ወይም በፖለቲካ ሊወገዱ የማይችሉት “ስግብግብነት፣ እርስ በእርስ አለመተማመንና ራስ ወዳድነት” መሆናቸውን በግልጽ ያብራራል። በተጨማሪም አምላክ በቅርቡ ክፋትን ከምድር ላይ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስወግድ ይገልጻል።

መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ስለያዘው ተስፋ ይበልጥ ለማወቅ ይፈልጋሉ? የይሖዋ ምሥክሮች አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹርና ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን በመጠቀም በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ቤታቸው ድረስ እየሄዱ መጽሐፍ ቅዱስን ያስተምራሉ። ይህ ብሮሹር:- አምላክ ማን ነው? አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው? የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የቤተሰብ ሕይወትን አስደሳች ሊያደርግልህ የሚችለው እንዴት ነው? እንደሚሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

የይሖዋ ምሥክሮች ቤትዎ መጥተው ስለ አምላክ ዓላማና ስለ መንግሥቱ እንዲያስተምሩዎት የሚፈልጉ ከሆነ ሊረዱዎት ፈቃደኛ ናቸው። እባክዎ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው ይላኩ።

□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ