የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g03 5/8 ገጽ 32
  • ለወጣቶች የሚሆን ጠቃሚ ምክር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለወጣቶች የሚሆን ጠቃሚ ምክር
  • ንቁ!—2003
ንቁ!—2003
g03 5/8 ገጽ 32

ለወጣቶች የሚሆን ጠቃሚ ምክር

አሜሪካ ውስጥ በካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖር ቢል የተባለ አንድ የይሖዋ ምሥክር ፍርድ ቤት አካባቢ መጽሔቶችን ሲያበረክት አንድ ሰው ወደ እርሱ መጥቶ የያዛቸውን የንቁ! መጽሔቶች በሙሉ እንዲያሳየው ጠየቀው። ቢል እንዲህ በማለት ያጋጠመውን ተናግሯል:- “በጉባኤያችን ያሉ አንዳንድ አስፋፊዎች የቆዩ መጽሔቶችን ሰጥተውኝ ስለነበር የተለያየ ዓይነት ርዕስ ያላቸው የንቁ! መጽሔቶችን አሳየሁት።

“ሰውዬው ፈጠን ብሎ መጽሔቶቹን ከተመለከተ በኋላ ያልደረሱትን መርጦ በአንድ ወገን ለያቸው። ከዚያም እነዚህን መጽሔቶች በሙሉ መውሰድ ይችል እንደሆነ ጠየቀኝ። በካሊፎርኒያ ግዛት ፍርድ ቤት ውስጥ እንደሚሠራና ለወጣት ጥፋተኞች የምክር አገልግሎት እንደሚሰጥ ነገረኝ። ንቁ! መጽሔቶችን የሚወስደው ‘ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች’ የሚለውን ዓምድ ፎቶ ኮፒ ለማድረግ እንደሆነ ገለጸልኝ። ከዚያም ፎቶ ኮፒ ያደረጋቸውን ርዕሶች በየርዕሳቸው እያደራጀ ያስቀምጥና ለሚመክራቸው ወጣቶች እንዲያነቡት ይሰጣቸው ነበር። ‘በዓምዱ ላይ የሚወጡት ርዕሰ ጉዳዮች ወጣቶች በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሟቸውን የተለመዱ ችግሮች የሚዳስሱ ናቸው’ አለኝና ወጣቶችን ለመርዳት እንዲህ ያሉ ጠቃሚ ጽሑፎችን ለሚያዘጋጁት ለይሖዋ ምሥክሮች ያለውን አድናቆት ገለጸልኝ። ወደፊት የሚወጡ የንቁ! መጽሔት እትሞችን በየጊዜው እንዳመጣለት ጠየቀኝ።”

“ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች” በተባለው ዓምድ ሥር በተከታታይ ከሚወጡት ትምህርቶች መካከል አብዛኞቹ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት ይችላሉ።

□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ