የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g17 ቁጥር 2 ገጽ 7
  • ንብ የምትፈልገው ቦታ ላይ ለማረፍ የምትጠቀምበት ዘዴ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ንብ የምትፈልገው ቦታ ላይ ለማረፍ የምትጠቀምበት ዘዴ
  • ንቁ!—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2017
  • የአንዳንድ ነፍሳት ዓይን
    ንቁ!—2008
  • አውሮፕላኑን በድንገት ማሳረፍ
    ንቁ!—2004
  • ብርሃን የሚያበሩ ፍጥረታት
    ንድፍ አውጪ አለው?
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2017
g17 ቁጥር 2 ገጽ 7
አንዲት ንብ አበባ ላይ ስታርፍ

ንድፍ አውጪ አለው?

ንብ የምትፈልገው ቦታ ላይ ለማረፍ የምትጠቀምበት ዘዴ

ንቦች በፈለጉት አቅጣጫ እየበረሩ መጥተው ያለምንም ችግር ማረፍ ይችላሉ። እንዲህ ያለ ችሎታ ሊኖራቸው የቻለው እንዴት ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ አንዲት ንብ ያለምንም ችግር የፈለገችበት ቦታ ላይ ማረፍ እንድትችል ወደምታርፍበት ቦታ የምትበርበትን ፍጥነት እየቀነሰች ሄዳ ዜሮ ማድረስ አለባት። ይህን ለማድረግ ደግሞ የምትበርበትን ፍጥነትና ከምታርፍበት ቦታ ያላትን ርቀት ማወቅ ይኖርባታል፤ ከዚያም እነዚህን ሁለት ነገሮች ግምት ውስጥ አስገብታ ፍጥነቷን እየቀነሰች መሄድ ያስፈልጋታል። ነገር ግን ንቦችን ጨምሮ አብዛኞቹ ነፍሳት ዓይኖቻቸው በጣም የተቀራረቡ ስለሆኑና ከርቀት አንጻር እይታቸውን ማስተካከል ስለማይችሉ በዓይኖቻቸው ርቀትን መለካት አይችሉም።

የሰው ልጆች ሁለት ዓይኖቻቸውን አቀናጅተው ስለሚጠቀሙ ከአንድ ነገር ያላቸውን ርቀት ማወቅ ይችላሉ፤ የንቦች እይታ ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው። ሆኖም ንቦች ወደ አንድ ነገር እየቀረቡ ሲሄዱ የዚያ ነገር መጠን እየጨመረ እንደሚመጣ ያውቃሉ። ወደ አንድ ነገር ይበልጥ በቀረቡ ቁጥር የዚያ ነገር መጠን የሚጨምርበት ፍጥነትም የዚያኑ ያህል ይጨምራል። በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አንዲት ንብ፣ የምታርፍበት ነገር መጠኑን የሚጨምርበት ፍጥነት ቋሚ ሆኖ እስኪታያት ድረስ የበረራ ፍጥነቷን እየቀነሰች ትሄዳለች። በመሆኑም የምታርፍበት ቦታ ጋ ስትደርስ ፍጥነቷ እየቀነሰ ሄዶ ዜሮ ይደርሳል፤ ይህም ያለምንም ችግር እንድታርፍ ያስችላታል።

ፕሮሲዲንግስ ኦቭ ዘ ናሽናል አካደሚ ኦቭ ሳይንስስ የተባለው መጽሔት እንዲህ በማለት ዘግቧል፦ “[ንቦች] የሚፈልጉበት ቦታ ላይ ለማረፍ የሚጠቀሙበት ይህ ዘዴ ቀላል ስለሆነ . . . በራሪ ሮቦቶችን የሚቆጣጠሩ ፕሮግራሞችን ለመሥራት ጥቅም ላይ ሊውል ይቻላል።”

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ንቦች የፈለጉበት ቦታ ላይ ያለምንም ችግር ለማረፍ የሚጠቀሙበት ዘዴ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ