የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሰይጣን ዲያብሎስ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
    • በነበረበት ምድር ተወስኖ ለሰዎች በማይታይ ሁኔታ ይኖራል ማለቱ አይደለም። “አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ” ከምድር ይርቃል። ራእይ 20:3 በሺው ዓመት መጨረሻ ላይ አሕዛብ ሳይሆኑ ሰይጣን ከጥልቁ ይፈታል ብሎ እንደሚናገር ልብ በል። ሰይጣን በሚፈታበት ጊዜ እነዚህ አሕዛብ ቀደም ብለው ዝግጁ ሆነው ይጠብቁታል።

      ኢሳይያስ 24:1–6 እና ኤርምያስ 4:23–29 ይህንን እምነት ይደግፋሉ ተብለው የሚጠቀሱበት ጊዜ አለ። እነዚህ ጥቅሶች እንዲህ ይላሉ:- “እነሆ፣ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፣ ባድማም ያደርጋታል፣ . . . ምድር መፈታትን ትፈታለች፣ ፈጽማም ትበላሻለች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና።” “ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ . . . አየሁ፣ እነሆም፣ ሰው አልነበረም፣ . . . እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል:- ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፤ . . . ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።” የእነዚህ ትንቢቶች ትርጉም ምንድን ነው? እነዚህ ትንቢቶች በመጀመሪያ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ላይ ተፈጽመዋል። ይሖዋ የቅጣት ፍርዱን ለመፈጸም ባቢሎናውያን ምድሪቱን እንዲወሩ አደረገ። በኋላም ባድማና ምድረ በዳ ሆነች። (በተጨማሪም ኤርምያስ 36:29⁠ን ተመልከት።) ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜ አምላክ መላዋን ምድር ባድማ ወይም ሰው አልባ አላደረጋትም። ወደ ፊትም ቢሆን እንዲህ አያደርግም። (በተጨማሪም “ምድር” በሚለው ሥር እንዲሁም በገጽ 113–115 ላይ “ሰማይ” የሚለውን ዋና ርዕስ ተመልከት።) ይሁን እንጂ የአምላክን ስም የምታሰድበውን የከዳተኛይቱ ኢየሩሳሌም አምሳያ የሆነችውን ሕዝበ ክርስትናን እና መላውን የሰይጣን የሚታይ ድርጅት ባድማ ያደርጋል።

      ሰይጣን በጥልቁ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ መላዋ ምድር በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ዘመን ባድማ ከመሆን ይልቅ ገነት ትሆናለች። (“ገነት” የሚለውን ተመልከት።)

  • የፆታ ግንኙነት
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
    • የፆታ ግንኙነት

      ፍቺ:- ሁለት ወላጆች ለመራባት የሚፈጽሙት የምድራዊ ፍጥረታት ባሕርይ ነው። በተባእትና በእንስት ፆታዎች መካከል ያለው ልዩነት በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ከመራባት የበለጠ ውጤት አስከትሏል። የሕይወት ምንጭ አምላክ ራሱ ስለሆነና የሰው ልጆችም የአምላክን ባሕርያት ማንጸባረቅ ስለሚኖርባቸው በፆታ ግንኙነት አማካኝነት ሕይወትን የማስተላለፍ ችሎታ በታላቅ አክብሮት መያዝ ይኖርበታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ