-
አይሁዳውያንከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
ሰው ባልንጀራውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን:- እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፣ ይላል እግዚአብሔር።” (ይህ ቃል ኪዳን የተገባው ከሥጋዊ እስራኤል ጋር ሳይሆን የሰማያዊ ሕይወት ተስፋ ካላቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሣዊ ተከታዮች ጋር ነው። ኢየሱስ የሞቱን መታሰቢያ ባቋቋመ ጊዜ ጽዋውን አንስቶ ለተከታዮቹ ሰጣቸውና እንዲህ አለ:- “ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።” [1 ቆሮ. 11:25])
ራእይ 7:4:- “የታተሙትንም ቁጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።” (በሚቀጥሉት ቁጥሮች ላይ ‘የሌዊ ነገድ’ እና ‘የዮሴፍ ነገድ’ ተጠቅሰዋል። እነዚህ ነገዶች ግን ከ12ቱ የሥጋዊ እስራኤል ነገዶች ዝርዝር ውስጥ የሉም ነበር። ከእያንዳንዱ ነገድ የመጡት ሰዎች ሁሉ ማኅተም እንደተደረገባቸው ሲናገር የዳንና የኤፍሬም ነገዶች ግን አልተጠቀሱም። [ከዘኁልቁ 1:4–16 ጋር አወዳድር።] ይህ ጥቅስ የሚናገረው ከክርስቶስ ጋር ሰማያዊ መንግሥት ይወርሳሉ በማለት ራእይ 14:1–3 ስለሚናገርላቸው የአምላክ መንፈሳዊ እስራኤል መሆን ይኖርበታል።)
ዕብ. 12:22:- “ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፣ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፣ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት [ደርሳችኋል።]” (ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያኖች የአምላክ ተስፋዎች ይፈጸሙባታል ብለው ተስፋ የሚያደርጉት “ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም” እንጂ ምድራዊቱ ኢየሩሳሌም አይደለችም።)
-
-
መንግሥትከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
መንግሥት
ፍቺ:- የአምላክ መንግሥት ይሖዋ የፍጥረታቱ ሁሉ ሉዓላዊ ገዥ መሆኑን የሚገልጽባት ወይም ይህን አጽናፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነቱን ለመግለጽ የሚጠቀምባት መሣሪያ ናት። በተለይ ይህ ቃል የአምላክ ሉዓላዊነት መግለጫ የሆነውን በልጁ በኩል የሚመራ ንጉሣዊ አገዛዝ ለማመልከት ተሠርቶበታል። “መንግሥት” የሚለው ቃል ንጉሥ ሆኖ የተቀባን ሰው አገዛዝ ወይም በዚያ ሰማያዊ አስተዳደር ሥር የሚገዛውን ምድራዊ ግዛት ሊገልጽ ይችላል።
-