የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሐሰተኛ ነቢያት
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
    • አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

      ‘የይሖዋ ምሥክሮች ሐሰተኛ ነቢያት ናቸው ብለው ቄሶች ነግረውናል’

      እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘አንድ ጥያቄ ብጠይቅዎትስ? በምን እንደምናምን ወይም ምን እንደምንሠራና በዚህም ምክንያት ሐሰተኛ ነቢያት መሆናችንን የሚያሳይ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሳይተዋችኋል? . . . መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛ ነቢያትን እንዴት አድርጎ እንደሚገልጻቸው ባሳይዎትስ? (በገጽ 133–136 ከተገለጹት ነጥቦች በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ ተጠቀም።)’

      ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘እንደዚህ የመሰለው ከባድ ክስ ግልጽ በሆነ መረጃ መደገፍ አለበት ቢባል እንደሚስማሙ እርግጠኛ ነኝ። ቄሶቹ እንደ ምሳሌ አድርገው የጠቀሱላችሁ ግልጽ የሆነ ነገር አለ? (የቤቱ ባለቤት ይፈጸማሉ ተብለው ሳይፈጸሙ ቀርተዋል የሚባሉ “ትንበያዎችን” የሚጠቅሱ ከሆነ በገጽ 135ና ከገጽ 136 መጀመሪያ እስከ ገጽ 137 መጨረሻ በቀረበው ሐሳብ ተጠቀም።)’

      ሌላ አማራጭ:- ‘አንድ ሰው እንደዚህ የመሰለ ክስ በእርስዎ ላይ ቢያቀርብ ቢያንስ አቋምዎን ወይም አመለካከትዎን ለመግለጽ አጋጣሚ ቢሰጥዎት በጣም ደስ እንደሚልዎት እርግጠኛ ነኝ፤ አይደለም እንዴ? . . . እንግዲያውስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ነገር ባሳይዎትስ . . . ?’

  • ዕድል
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
    • ዕድል

      ፍቺ:- መፈጸሙ የማይቀርና ብዙ ጊዜ መጥፎ ውጤት የሚያስከትል ነገር ነው። ማንኛውም ነገር በመለኮታዊ ፈቃድ ወይም ከሰው በላይ በሆነ ኃይል የተወሰነ ነው፤ ማንኛውም ነገር የሚፈጸመው አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት ነው የሚል እምነት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም።

      እያንዳንዱ ሰው ‘የሚሞትበት ጊዜ’ አስቀድሞ የተወሰነ ነውን?

      ይህ እምነት በግሪኮችና በሮማውያን ዘንድ በሠፊው ተቀባይነት ያገኘነበር። አረማውያን በነበሩት ግሪካውያን አፈታሪክ መሠረት ዕድል የሕይወትን ክር የምትፈትል፣ ርዝመቱን የምትወስንና የምትቆርጥ የሦስት አማልክት ጥምረት ናት።

      መክብብ 3:1, 2 “ለመሞትም ጊዜ አለው” በማለት ይናገራል። ነገር ግን ይህ ለግለሰቡ አስቀድሞ የተወሰነና የተቆረጠ ጊዜ አለመሆኑን ለማሳየት መክብብ 7:17 እንዲህ በማለት ይመክራል:- “እጅግ ክፉ አትሁን፣ እልከኛም አትሁን፣ ጊዜህ ሳይደርስ እንዳትሞት። ” (ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።) ምሳሌ 10:27 “የኀጥኣን ዕድሜ ግን ታጥራለች” ይላል። መዝሙር 55:23​ም በተጨማሪ “የደም ሰዎችና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ አይሞላም” ይላል። ታዲያ የ⁠መክብብ 3:1, 2 ትርጉም ምንድን ነው? በዚህ ፍጽምና በጐደለው ሥርዓት ውስጥ ሕይወትና ሞት የማያቋርጥ ዑደት እንዳላቸው መግለጹ ነው። ሰዎች የሚወለዱበትና የሚሞቱበት ጊዜ አላቸው። ይህም ብዙ ጊዜ ከ70 ወይም ከ80 ዓመት ያልበለጠ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ከዚህ ሊቀድም ወይም ሊዘገይ ይችላል።—መዝ. 90:10፤ በተጨማሪ መክብብ 9:11 አዓት ተመልከት።

      የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ርዝመትና አሟሟት ገና ሲወለድ ወይም ከዚያ ቀደም ብሎ የተወሰነ ከሆነ ከአደገኛ ሁኔታዎች መራቅ ወይም ጤንነትን መንከባከብ እና አደጋ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ ሞትን ስለማያስቀር አስፈላጊ አይሆንም ነበር። ጦርነት የሚደረግበት አካባቢ ከጦርነት ክልል ርቆ ከሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ የባሰ አደጋ የለውም ብለው ያምናሉን? ስለ ጤንነትዎ ይጠነቀቃሉ? ልጆችዎንስ ወደ ሐኪም ይወስዳሉ? ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በአማካይ ከማያጨሱ ሰዎች ሦስት ወይም አራት ዓመት ቀድመው የሚሞቱት ለምንድን ነው? በመኪና የሚሳፈሩ ሰዎች ከመቀመጫው ጋር የተያያዘውን ቀበቶ ሲታጠቁና መኪና አሽከርካሪዎችም የትራፊክ ሕጐችን ሲያከብሩ የመኪና አደጋ የሚቀንሰው ለምንድን ነው? ጥንቃቄ ማድረግ ጥቅም ያለው መሆኑ ግልጽ ነው።

      የሚፈጸም ነገር ሁሉ “የአምላክ ፈቃድ” ነውን?

      2 ጴጥ. 3:9:- “ሁሉ ወደ ንሥሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።” (ነገር ግን ትዕግሥቱን አይተው የሚለወጡት ሁሉም ሰዎች አይደሉም። አንዳንዶች ንስሐ ሳይገቡ መቅረታቸው “የአምላክ ፈቃድ” እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ከ⁠ራእይ 9:20, 21 ጋር አወዳድር።)

      ኤር. 7:23–26:- “ቃሌን ስሙ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር [እስራኤላውያንን] አዘዝኋቸው። ነገር ግን . . . አልሰሙም። . . . በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።” (በእስራኤል ምድር ይፈጸም የነበረው መጥፎ ሥራ ሁሉ “የአምላክ ፈቃድ” እንዳልነበረ ግልጽ ነው።)

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ