-
ቅዱሳንከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
የሚገኙ መሆናቸውና ይህ በእኛ ላይ የሚኖረው ውጤት ነው። አይመስልዎትም? . . . ስለ እነዚህ ቅዱሳን በዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጥሩ ነጥብ አግኝቻለሁ። ለእርስዎም ባካፍልዎት ደስ ይለኛል። (ራእይ 5:9, 10)’ [ማስታወሻ:- በእንግሊዝኛ በጥቅሱ አባባል ላይ ጥያቄ ከተነሣ ቀጥሎ ባለው ሐሳብ መጠቀም ይቻላል:- ጀባ “ዓለምን ይገዛሉ” ይላል። ኮክ “በምድር ላይ ይገዛሉ” ይላል። ኖክስ ደግሞ “በምድር ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ” ሲል ይገልጻል። ኒአባ እና ዱዌይ ግን “በምድር ላይ ሆነው ይገዛሉ” ይላሉ። በግሪክኛው ሰዋስው ላይ የተሰጠውን ሐሳብ “ሰማይ” በሚለው ሥር በገጽ 168 ላይ ተመልከት።] (2) ‘እንዲህ ባለው መስተዳድር ሥር ሕይወት ምን ይመስል ይሆን? (ራእይ 21:2–4)’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ (በፊት ካቶሊክ ከነበርክ):- ‘ለብዙ ዓመታት የቅዱሳንን በዓላት አከብርና ለእነርሱም እጸልይ ነበር። ግን በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አደርግ ስለነበረው ነገር እንድመረምር ያደረገኝ ጥቅስ አገኘሁ። እስቲ ላሳይዎት። (ገጽ 352ን ተመልከት።)’
-
-
መዳንከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
መዳን
ፍቺ:- ከጥፋት ወይም ከአደጋ መትረፍ ወይም መላቀቅ ማለት ነው። ሰዎቹ የሚላቀቁት ከጨቋኞች ወይም ከአሳዳጆች እጅ ሊሆን ይችላል። ይሖዋ እውነተኛ ክርስቲያኖችን በሙሉ በልጁ አማካኝነት ከአሁኑ የነገሮች ሥርዓት ያላቅቃቸዋል፤ እንዲሁም ከኃጢአትና ከሞት ያድናቸዋል። በዚህ “በመጨረሻው ቀን” የሚኖሩና የታመኑ የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎች የሚያገኙት መዳን ከታላቁ መከራ መትረፍን ይጨምራል።
አምላክ በታላቅ ምሕረቱ ውሎ አድሮ የሰው ልጆችን በሙሉ ያድናልን?
2 ጴጥሮስ 3:9 አጠቃላይ የሆነ መዳን እንደሚኖር ያመለክታልን? ጥቅሱ እንዲህ ይላል:- “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፣ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።” የአዳም ልጆች በሙሉ ንስሐ እንዲገቡ የመሐሪው አምላክ ፈቃድ ከመሆኑም በላይ ንስሐ የገቡ ሁሉ የኃጢአት ሥርየት የሚያገኙበትን መንገድ በልግስና አዘጋጅቷል። ይሁን እንጂ አምላክ ይህንን ዝግጅት እንዲቀበል ማንንም ሰው አያስገድድም። (ከዘዳግም 30:15–20 ጋር አወዳድር።) ብዙዎች ይህንን ዝግጅት አይቀበሉም። ወንዝ ውስጥ ሊሰምጥ ተቃርቦ ሳለ ሊረዳው የፈለገው ሰው ሕይወቱን ሊያድንለት
-