የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 103 ገጽ 238-ገጽ 239 አን. 2
  • “መንግሥትህ ይምጣ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “መንግሥትህ ይምጣ”
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በችግር የተሞላ ኑሮ ተጀመረ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ በቅርቡ ይፈጸማል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 103 ገጽ 238-ገጽ 239 አን. 2
ልጆችና ትላልቅ ሰዎች በገነት ውስጥ ተደስተው ሲኖሩ

ትምህርት 103

“መንግሥትህ ይምጣ”

ይሖዋ እንዲህ በማለት ቃል ገብቷል፦ ‘ከዚህ በኋላ ለቅሶ፣ ሥቃይ፣ ሕመም ወይም ሞት አይኖርም። እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ላይ እጠርጋለሁ። በፊት የነበሩ መጥፎ ነገሮች በሙሉ ይረሳሉ።’

ይሖዋ አዳምንና ሔዋንን በኤደን ገነት ያስቀመጣቸው በሰላምና በደስታ እንዲኖሩ ነበር። የሰማዩን አባታቸውን እንዲያመልኩ እንዲሁም ልጆች ወልደው ምድርን እንዲሞሉ አስቦ ነበር። አዳምና ሔዋን በይሖዋ ላይ ዓመፁ፤ ሆኖም የይሖዋ ዓላማ አልተለወጠም። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንደተመለከትነው አምላክ የገባውን ቃል በሙሉ ይፈጽማል። ይሖዋ ለአብርሃም ቃል በገባው መሠረት በሰማይ ያለው መንግሥቱ በምድር ላይ አስደሳች በረከቶችን ያመጣል።

ልጆች፣ ትላልቅ ሰዎችና የዱር እንስሳት በገነት ውስጥ አብረው ሲኖሩ

በቅርቡ ሰይጣን፣ አጋንንቱና ክፉ ሰዎች በሙሉ ይጠፋሉ። በሕይወት ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ይሖዋን ያመልካሉ። ማንኛችንም ብንሆን አንታመምም እንዲሁም አንሞትም። ከዚህ ይልቅ በየቀኑ ጠዋት ኃይላችን ታድሶ እንነሳለን፤ ሕይወት አስደሳች ይሆንልናል። ምድር ገነት ትሆናለች። ሁሉም ሰው ጥሩ ምግብና ምቹ የሆነ ቤት ይኖረዋል። ጨካኝ ወይም ዓመፀኛ የሆኑ ሰዎች አይኖሩም፤ ከዚህ ይልቅ ሁሉም ሰው ደግና አሳቢ ይሆናል። በዚያን ጊዜ የዱር እንስሳት ከእኛ አይሸሹም፤ እኛም እነሱን አንፈራቸውም።

ይሖዋ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳት ሲጀምር የሚኖረውን ደስታ ለማሰብ ሞክር! በጥንት ዘመን የኖሩ እንደ አቤል፣ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ሣራ፣ ሙሴ፣ ሩት፣ አስቴርና ዳዊት ያሉ ሰዎች ከሞት ሲነሱ እንቀበላቸዋለን። እነሱም ምድርን ገነት በማድረጉ ሥራ አብረውን ይካፈላሉ። በዚያን ጊዜ የምንሠራው ብዙ አስደሳች ሥራ ይኖረናል።

ይሖዋ አንተም በገነት ውስጥ እንድትኖር ይፈልጋል። ያን ጊዜ ስለ ይሖዋ ያለህ እውቀት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል። አሁንም ሆነ ለዘላለም በየዕለቱ ወደ ይሖዋ መቅረባችንን እንቀጥል!

“ይሖዋ አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ . . . ግርማ፣ ክብርና ኃይል ልትቀበል ይገባሃል።”—ራእይ 4:11

ጥያቄ፦ የአምላክ መንግሥት ምድርን በሚገዛበት ወቅት የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት ይኖራቸዋል? በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰዎች መካከል በገነት ውስጥ ማግኘት የምትፈልገው ማንን ነው?

ራእይ 21:3, 4፤ ኢዮብ 33:25፤ ምሳሌ 2:21, 22፤ ኢሳይያስ 11:2-10፤ 33:24፤ 65:21፤ ማቴዎስ 6:9, 10፤ ዮሐንስ 5:28, 29፤ 17:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ