የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 29
  • ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቅዱሳን
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይኖርብናል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ወደ “ቅዱሳን” መጸለይ ተገቢ ነው?
    ንቁ!—2010
  • እውነተኞቹ ቅዱሳን ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 29

ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

እንዲህ ማድረግ ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ በኢየሱስ ስም ለአምላክ ብቻ መጸለይ እንዳለብን ይገልጽልናል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል፦ “እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።’” (ማቴዎስ 6:9 አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅዱሳን፣ ወደ መላእክት ወይም ከአምላክ ውጪ ወደ ሌላ አካል እንዲጸልዩ አላዘዛቸውም።

በተጨማሪም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል፦ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14:6 አ.መ.ት) አምላክ አማላጅ እንዲሆን አድርጎ የሾመው ኢየሱስን ብቻ ነው።​—ዕብራውያን 7:25

ወደ አምላክ መጸለዬ እንዳለ ሆኖ ወደ ቅዱሳንም ጭምር ብጸልይስ?

አምላክ አሥርቱን ትእዛዛት ሲሰጥ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ . . . ቀናተኛ አምላክ ነኝ” ብሏል። (ዘፀአት 20:5 አ.መ.ት) ይሁንና አምላክ “ቀናተኛ” የሆነው እንዴት ነው? የማጥኛ ጽሑፍ ያለው አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግርጌ ማስታወሻው ላይ እንደሚናገረው “ቀናተኛ” ሲባል “እርሱን ብቻ ማምለክን ይጠይቃል።” በመሆኑም አምላክ ጸሎትን ጨምሮ ከአምልኮ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ነገሮች ለእሱ ብቻ እንድናቀርብ ይፈልጋል።—ኢሳይያስ 48:11

ከእሱ ውጪ ሌላው ቀርቶ ለቅዱሳንና ለመላእክትም ብንጸልይ አምላክ ያዝንብናል። ሐዋርያው ዮሐንስ ለአንድ መልአክ የአምልኮ ስግደት ሊያቀርብለት ሲል መልአኩ እንደሚከተለው በማለት አስቁሞታል፦ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ።”​—ራእይ 19:10 አ.መ.ት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ