ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 51-52
የይሖዋ ቃል አንድም ሳይቀር ይፈጸማል
ይሖዋ ወደፊት የሚፈጸሙ ነገሮችን በትክክል ተናግሯል
የፋርስ ንጉሣዊ ዘብ ቀስተኛ
“ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ”
ሜዶናውያንና ፋርሳውያን የተዋጣላቸው ቀስተኞች የነበሩ ሲሆን በዋነኝነት የሚጠቀሙበት መሣሪያም ቀስት ነበር። ፍላጻዎቻቸውን የሚያሾሉት፣ የጠላታቸው ሰውነት ውስጥ ጠልቀው እንዲገቡ ለማድረግ ሲሉ ነበር
“የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋት አቁመዋል”
የናቦኒደስ ዜና መዋዕል እንደሚገልጸው “የቂሮስ ወታደሮች ወደ ባቢሎን የገቡት ያለ ጦርነት ነው።” ይህም ኤርምያስ ከተናገረው ትንቢት ጋር የሚስማማ ነው
የናቦኒደስ ዜና መዋዕል
“ባቢሎንም የድንጋይ ቁልል [እንዲሁም] ለዘላለም ባድማ” ትሆናለች
ከ539 ዓ.ዓ. አንስቶ ባቢሎን ቀድሞ የነበራትን ክብር ማጣት ጀመረች። ታላቁ እስክንድር፣ ባቢሎንን ዋና ከተማው ሊያደርጋት አስቦ የነበረ ቢሆንም በድንገት ሞተ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን በባቢሎን የሚኖር የአይሁድ ማኅበረሰብ ነበረ፤ በዚህም ምክንያት ሐዋርያው ጴጥሮስ ወደ ባቢሎን ሄዷል። በአራተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ግን ከተማዋ ፈራርሳ ነበር፤ ውሎ አድሮም ሙሉ በሙሉ ጠፋች