የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 8 ገጽ 26
  • አብርሃምና ሣራ አምላክን ታዘዋል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አብርሃምና ሣራ አምላክን ታዘዋል
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አብርሃም ማን ነበር?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የአምላክ ወዳጅ የሆነው አብርሃም
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • አብርሃም እና ሣራ—እምነታቸውን መኮረጅ ትችላለህ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ይሖዋ “ወዳጄ” በማለት ጠርቶታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 8 ገጽ 26
አብርሃምና ሣራ ዑርን ለቅቀው ለመውጣት ዕቃቸውን ሲያዘጋጁ

ትምህርት 8

አብርሃምና ሣራ አምላክን ታዘዋል

በባቤል አቅራቢያ የምትገኝ ዑር የምትባል አንዲት ከተማ ነበረች፤ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ይሖዋን ሳይሆን ሌሎች አማልክትን ያመልኩ ነበር። ሆኖም በዚህች ከተማ የሚኖር ይሖዋን ብቻ የሚያመልክ አንድ ሰው ነበር። ይህ ሰው አብርሃም ይባላል።

ይሖዋ አብርሃምን ‘ቤትህንና ዘመዶችህን ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ’ አለው። ከዚያም አምላክ እንዲህ ብሎ ቃል ገባለት፦ ‘ብዙ ሕዝብ ትሆናለህ፤ እንዲሁም በአንተ አማካኝነት ለምድር ሕዝቦች ሁሉ ጥሩ ነገር አደርግላቸዋለሁ።’

አብርሃም፣ ይሖዋ ወዴት እንደሚልከው ባያውቅም በይሖዋ ታምኗል። ስለዚህ አብርሃም፣ ሚስቱ ሣራ፣ አባቱ ታራ እንዲሁም የወንድሙ ልጅ ሎጥ ዕቃቸውን ይዘው በታዛዥነት ረጅሙን ጉዞ ጀመሩ።

አብርሃምና ቤተሰቡ ይሖዋ ሊያሳያቸው ወደፈለገው ቦታ ሲደርሱ አብርሃም 75 ዓመቱ ነበር። ያ ቦታ የከነአን ምድር ይባል ነበር። እዚያ ከደረሱ በኋላ አምላክ አብርሃምን አነጋገረው፤ ‘ይህን የምታየውን ቦታ ሁሉ ለልጆችህ እሰጣቸዋለሁ’ ብሎ ቃል ገባለት። አብርሃምና ሣራ ግን አርጅተው የነበረ ሲሆን ምንም ልጅ አልነበራቸውም። ታዲያ ይሖዋ የገባውን ቃል የሚፈጽመው እንዴት ነው?

አብርሃምና ሣራ ወደ ከነአን ሲጓዙ

“አብርሃም . . . ወደፊት ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ በመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን ስፍራ ለቆ ወጣ።”—ዕብራውያን 11:8

ጥያቄ፦ ይሖዋ አብርሃምን ምን እንዲያደርግ ጠየቀው? ይሖዋ ለአብርሃም ምን ብሎ ቃል ገባለት?

ዘፍጥረት 11:29–12:9፤ የሐዋርያት ሥራ 7:2-4፤ ገላትያ 3:6፤ ዕብራውያን 11:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ