የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 3 ገጽ 8-9
  • ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ነበራት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ነበራት
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ረዓብ ዜናውን ሰምታ ነበር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ረዓብ ሰላዮቹን ደበቀች
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ረዓብ “በሥራ ጻድቅ ተብላ” ተጠርታለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ረዓብ በእምነት በሠራችው ሥራ ጻድቅ ሆና ተቆጠረች
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 3 ገጽ 8-9
ረዓብ ሰላዮቹ ወደተደበቁበት ጣሪያ ወጣች

ትምህርት 3

ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ነበራት

በኢያሪኮ ከተማ እንደምንኖር አድርገን እናስብ። ይህች ከተማ የምትገኘው በከነዓን ምድር ነው፤ በዚያ የሚኖሩት ሰዎች በይሖዋ አያምኑም። ረዓብ የተባለች አንዲት ሴት በዚያች ከተማ ውስጥ ትኖር ነበር።

ረዓብ፣ ልጅ እያለች ሙሴ በባርነት ሥር የነበሩትን እስራኤላውያን ከግብፅ እየመራ እንዳወጣቸውና ቀይ ባሕርን ከፍሎ እንዳሻገራቸው ሰምታ ነበር። በተጨማሪም እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው ጋር ባካሄዱት ጦርነት ድል እንዲያደርጉ ይሖዋ እንደረዳቸው ሰምታለች። አሁን ደግሞ ረዓብ፣ እስራኤላውያን ኢያሪኮ አቅራቢያ እንደሰፈሩ ሰማች!

ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ስለነበራት ሰላዮቹን ጠላቶቻቸው እንዳይዟቸው ረድታቸዋለች

አንድ ቀን ምሽት፣ ሁለት እስራኤላውያን ከተማዋን ለመሰለል ወደ ኢያሪኮ ሄዱ። ሰላዮቹ ወደ ረዓብ ቤት መጡ። እሷም እንዲገቡ ጋበዘቻቸው። ሌሊት ላይ የኢያሪኮ ንጉሥ፣ እስራኤላውያን ሰላዮች ወደ ከተማዪቱ እንደገቡና ረዓብ ቤት እንዳረፉ ሰማ። በመሆኑም ንጉሡ፣ ሰላዮቹን ለመያዝ መልእክተኞችን ላከ። ረዓብ ሰላዮቹን ጣሪያ ላይ ከደበቀቻቸው በኋላ ለንጉሡ መልእክተኞች እንዲህ አለቻቸው፦ ‘ሰላዮቹ ወደ እኔ መጥተው ነበር፤ አሁን ግን ከከተማዋ ወጥተው ሄደዋል። ቶሎ ከተከተላችኋቸው ልትይዟቸው ትችላላችሁ!’ ረዓብ ሰላዮቹን በጠላቶቻቸው ከመያዝ ያዳነቻቸው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?— ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ስለነበራት እንዲሁም ይሖዋ የከነዓንን ምድር ለእስራኤላውያን እንደሚሰጣቸው ታውቅ ስለነበረ ነው።

ሰላዮቹም ከረዓብ ቤት ከመውጣታቸው በፊት፣ ኢያሪኮ ስትጠፋ እሷና ቤተሰቧ እንደሚድኑ ቃል ገቡላት። ረዓብ ከጥፋቱ ለመዳን ምን እንድታደርግ እንደነገሯት ታውቃለህ?— እንዲህ አሏት፦ ‘ይህን ቀይ ገመድ በመስኮትሽ ላይ አንጠልጥዪው፤ እንዲህ ካደረግሽ ቤትሽ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ይተርፋል።’ ረዓብም ልክ ሰላዮቹ እንደነገሯት አደረገች። ከዚያ በኋላ ምን እንደተፈጸመ ታውቃለህ?—

ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ስለነበራት ሰላዮቹን ጠላቶቻቸው እንዳይዟቸው ረድታቸዋለች

ይሖዋ ረዓብንና ቤተሰቦቿን አድኗቸዋል

ከጥቂት ቀናት በኋላ እስራኤላውያን ኢያሪኮን ይዞሯት ጀመር። ለስድስት ቀናት ያህል በቀን አንድ ጊዜ ከተማዪቱን የዞሯት ሲሆን ይህን ሲያደርጉ ምንም ድምፅ አላሰሙም ነበር። በሰባተኛው ቀን ግን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሯት። ከዚያም ሁሉም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ። በዚህ ጊዜ ይሖዋ የከተማይቱ ግንብ እንዲፈርስ አደረገ። ይሁን እንጂ ቀይ ፈትል በመስኮቱ ላይ የተንጠለጠለበት ቤት ምንም አልሆነም! ሥዕሉ ላይ ይህ ቤት ይታይሃል?— ረዓብና ቤተሰቦቿ ከጥፋት ተረፉ!

ከረዓብ ምን ትምህርት እናገኛለን?— ረዓብ፣ ይሖዋ ስላደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች የሰማችው ታሪክ በእሱ ላይ እምነት እንዲኖራት ረድቷታል። አንተም ስለ ይሖዋ በርካታ አስደናቂ ነገሮችን እየተማርክ ነው። ታዲያ አንተስ እንደ ረዓብ በአምላክ ላይ እምነት አለህ?— እንዲህ ያለ እምነት እንዳለህ ምንም ጥርጥር የለውም!

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • ኢያሱ 2:1-24፤ 6:1-5, 14, 15, 20-25

  • ዕብራውያን 11:31

ጥያቄዎች፦

  • ረዓብ ልጅ እያለች የትኛውን ታሪክ ሰምታ ነበር?

  • ረዓብ፣ እስራኤላውያኑን ሰላዮች የረዳቻቸው እንዴት ነው? እንዲህ ያደረገችውስ ለምንድን ነው?

  • ሰላዮቹ፣ ለረዓብ ምን ቃል ገቡላት?

  • ከረዓብ ምን ትምህርት ታገኛለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ