የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 8 ገጽ 18-19
  • ኢዮስያስ ጥሩ ጓደኞች ነበሩት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢዮስያስ ጥሩ ጓደኞች ነበሩት
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢዮስያስ ትክክል የሆነውን ለማድረግ መርጧል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ትሑት የነበረው ኢዮስያስ የይሖዋን ሞገስ አግኝቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የመጨረሻው የእስራኤል ጥሩ ንጉሥ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 8 ገጽ 18-19
ንጉሥ ኢዮስያስ ጓደኛውን ኤርምያስን ሲሰማው

ትምህርት 8

ኢዮስያስ ጥሩ ጓደኞች ነበሩት

ትክክል የሆነውን ማድረግ ከባድ እንደሆነ ይሰማሃል?— ብዙ ሰዎች እንደዚያ ይሰማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢዮስያስ የተባለ አንድ ልጅ ትክክል የሆነውን ማድረግ ከባድ ሆኖበት እንደነበር ይናገራል። ደስ የሚለው ግን ትክክል የሆነውን እንዲያደርግ የረዱት ጥሩ ጓደኞች ነበሩት። እስቲ ስለ ኢዮስያስና ስለ ጓደኞቹ እንመልከት።

የኢዮስያስ አባት የይሁዳ ንጉሥ የሆነው አሞን ነው። አሞን በጣም መጥፎ ሰው ሲሆን ጣኦት ያመልክ ነበር። ኢዮስያስ አባቱ ሲሞት የይሁዳ ንጉሥ ሆነ። በወቅቱ ገና ስምንት ዓመቱ ነበር። ታዲያ ኢዮስያስ እንደ አባቱ መጥፎ ሰው የሆነ ይመስልሃል?— በፍጹም!

ነቢዩ ሶፎንያስ ይሖዋ ለይሁዳ ሕዝብ የላከውን መልእክት ሲያውጅ

ሶፎንያስ ሕዝቡ ጣኦት እንዳያመልኩ አስጠንቅቆ ነበር

ኢዮስያስ ትንሽ ልጅ እያለም እንኳ ይሖዋን የመታዘዝ ፍላጎት ነበረው። በመሆኑም ጓደኛ አድርጎ የመረጠው ይሖዋን የሚወዱ ሰዎችን ብቻ ነው። እነሱም ትክክል የሆነውን እንዲያደርግ ረድተውታል። ከኢዮስያስ ጓደኞች መካከል አንዳንዶቹ እነማን ነበሩ?

ከጓደኞቹ አንዱ ሶፎንያስ ነው። ሶፎንያስ ነቢይ ሲሆን የይሁዳ ነዋሪዎች ጣኦት የሚያመልኩ ከሆነ መጥፎ ነገር እንደሚደርስባቸው ነግሯቸው ነበር። ኢዮስያስ የሶፎንያስን ማስጠንቀቂያ ሰምቷል፤ በመሆኑም የሚያመልከው ጣኦታትን ሳይሆን ይሖዋን ነበር።

ሌላው የኢዮስያስ ጓደኛ ደግሞ ኤርምያስ ነው። ኤርምያስና ኢዮስያስ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የነበሩ ሲሆን ያደጉትም በአንድ አካባቢ ነው። በጣም የሚቀራረቡ ጓደኛሞች ስለነበሩ ኢዮስያስ በሞተበት ወቅት ኤርምያስ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ለመግለጽ የለቅሶ ግጥም ጽፎ ነበር። ኤርምያስና ኢዮስያስ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ እንዲሁም ይሖዋን ለመታዘዝ እንዲችሉ አንዳቸው ሌላውን ያበረታቱ ነበር።

ኢዮስያስና ኤርምያስ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ እንዲችሉ አንዳቸው ሌላውን ያበረታቱ ነበር

ከኢዮስያስ ታሪክ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?— ኢዮስያስ ገና ትንሽ ልጅ እያለም እንኳ ትክክል የሆነውን ለማድረግ ይፈልግ ነበር። ጓደኝነት መመሥረት ያለበት ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር እንደሆነ ያውቅ ነበር። አንተም ይሖዋን የሚወዱና ትክክል የሆነውን እንድታደርግ የሚረዱህ ጓደኞች እንድትመርጥ እናበረታታሃለን!

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • 2 ዜና መዋዕል 33:21-25፤ 34:1, 2፤ 35:25

ጥያቄዎች፦

  • የኢዮስያስ አባት ማን ነው? ትክክል የሆነውን ነገር ያደርግ ነበር?

  • ኢዮስያስ ገና ትንሽ ልጅ እያለም እንኳ ምን ማድረግ ይፈልግ ነበር?

  • ከኢዮስያስ ጓደኞች መካከል ሁለቱ እነማን ናቸው?

  • ከኢዮስያስ ምሳሌ ምን ትምህርት ታገኛለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ