የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 7 ገጽ 16-17
  • ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • እንደ ኤልያስ ታማኝ ትሆናላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 7 ገጽ 16-17
ብቸኝነትና ፍርሃት የተሰማው ትንሽ ልጅ

ትምህርት 7

ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?

በሥዕሉ ላይ ያለውን ትንሽ ልጅ አየኸው? ብቻውን ከመሆኑም ሌላ የፈራ ይመስላል አይደል? አንተስ እንዲህ ተሰምቶህ ያውቃል?— ሁሉም ሰው አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ይሰማዋል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አንዳንድ የይሖዋ ወዳጆችም ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቷቸው እንደሚያውቅ ይናገራል። ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ኤልያስ ነው። እስቲ የኤልያስን ታሪክ እንመልከት።

ንግሥት ኤልዛቤል በቁጣ ስትጮኽ

ኤልዛቤል ኤልያስን ለመግደል ፈልጋ ነበር

ኤልያስ፣ ኢየሱስ ከመወለዱ ከረጅም ጊዜ በፊት በእስራኤል ይኖር ነበር። በወቅቱ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው አክዓብ፣ እውነተኛ አምላክ የሆነውን ይሖዋን የሚያገለግል ሰው አልነበረም። አክዓብና ሚስቱ ኤልዛቤል የሚያመልኩት በኣል የተባለውን የሐሰት አምላክ ነበር። በመሆኑም አብዛኞቹ እስራኤላውያን በኣልን ማምለክ ጀመሩ። በጣም መጥፎ ሴት የነበረችው ንግሥት ኤልዛቤል፣ ኤልያስን ጨምሮ ይሖዋን የሚያገለግሉ ሰዎችን በሙሉ ለመግደል ትፈልግ ነበር። በዚህ ጊዜ ኤልያስ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ?—

ኤልያስ መኖሪያውን ትቶ ሸሸ! ረጅም ርቀት ተጉዞ ወደ በረሃ በመሄድ በአንድ ዋሻ ውስጥ ተደበቀ። ይህን ያደረገው ለምን ይመስልሃል?— አዎ፣ በጣም ፈርቶ ስለነበር ነው። ይሁን እንጂ ኤልያስ መፍራት አልነበረበትም። ለምን? ምክንያቱም ይሖዋ ሊረዳው እንደሚችል ያውቅ ነበር። ይሖዋ ምን ያህል ኃይል እንዳለው ከዚህ ቀደም ለኤልያስ አሳይቶታል። በአንድ ወቅት ይሖዋ፣ ኤልያስ ላቀረበው ጸሎት ምላሽ በመስጠት እሳት ከሰማይ እንዲወርድ አድርጎ ነበር። አሁንም ቢሆን ይሖዋ፣ ኤልያስን ሊረዳው እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም!

ይሖዋ ከሰማይ እሳት በማውረድ ለኤልያስ ጸሎት ምላሽ ሰጠ፤ ኤልያስ በዋሻ ውስጥ፤ ኤልያስ፣ ይሖዋ ካበረታታው በኋላ ተደስቶ

ይሖዋ ኤልያስን የረዳው እንዴት ነው?

ኤልያስ ዋሻው ውስጥ እያለ ይሖዋ ‘እዚህ ምን ታደርጋለህ?’ በማለት ጠየቀው። ኤልያስም ‘አንተን ከሚያመልኩት መካከል የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ። እኔም እንዳልገደል ፈርቻለሁ’ በማለት መለሰ። ኤልያስ ሌሎቹ የይሖዋ አገልጋዮች በሙሉ እንደተገደሉ አስቦ ነበር። ይሖዋ ግን እንዲህ አለው፦ ‘የቀረኸው አንተ ብቻ አይደለህም። አሁንም እኔን የሚያገለግሉ 7,000 ሰዎች አሉኝ። አትፍራ። ብዙ የምትሠራው ሥራ አዘጋጅቼልሃለሁ!’ ኤልያስ ይህንን ሲሰማ የተደሰተ ይመስልሃል?—

ኤልያስ ካጋጠመው ሁኔታ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?— ምንም ነገር ቢያጋጥምህ ብቸኝነትና ፍርሃት ሊሰማህ አይገባም። አንተንም ሆነ ይሖዋን የሚወዱ ወዳጆች አሉህ። በተጨማሪም፣ ይሖዋ ከፍተኛ ኃይል ስላለው ምንጊዜም ይረዳሃል! መቼም ቢሆን ብቻህን እንዳልሆንክ ማወቅህ አያስደስትህም?—

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • 1 ነገሥት 19:3-18

  • መዝሙር 145:18

  • 1 ጴጥሮስ 5:9

ጥያቄዎች፦

  • በኤልያስ ዘመን አብዛኞቹ እስራኤላውያን ይሖዋን ያመልኩ ነበር? የሚያመልኩት ማንን ነበር?

  • ኤልያስ ሸሽቶ በዋሻ ውስጥ የተደበቀው ለምንድን ነው?

  • ይሖዋ ኤልያስን ምን አለው?

  • ኤልያስ ካጋጠመው ነገር ምን ትምህርት እናገኛለን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ