የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | መስከረም 15
    • 3, 4. (ሀ) አምላክ ለአዳምና ለሔዋን ምን ትእዛዝ ሰጣቸው? (ለ) ይህንን መመሪያ መታዘዛቸው ምን ያህል አስፈላጊ ነበር?

      3 አዳምና ሔዋን ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ ቢዘረጋላቸውም የማይሞት ሕይወት አልነበራቸውም። በሕይወት ለመኖር መተንፈስ፣ መብላትና መጠጣት እንዲሁም መተኛት ነበረባቸው። ከሁሉ በላይ ግን በሕይወት መኖራቸው የተመካው ሕይወት ከሰጣቸው አካል ጋር ባላቸው ዝምድና ላይ ነበር። (ዘዳ. 8:3) ሕይወትን ማጣጣማቸውን እንዲቀጥሉ የአምላክን መመሪያ የግድ መከተል ነበረባቸው። ይሖዋ፣ ሔዋን ከመፈጠሯ በፊት እንኳ ይህንን ለአዳም ግልጽ አድርጎለታል። እንዴት? “እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ ‘በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።’”—ዘፍ. 2:16, 17

      4 ‘መልካምና ክፉን የሚያሳውቀው ዛፍ’ የሚያመለክተው አምላክ፣ መልካም ወይም ክፉ የሚባለው ምን እንደሆነ ለመወሰን ያለውን መብት ነው። እርግጥ ነው፣ አዳም ጥሩ ወይም መጥፎ የሚባለው ምን እንደሆነ ያውቅ ነበር፤ ምክንያቱም በአምላክ መልክ የተፈጠረ ከመሆኑም ሌላ ሕሊና አለው። ዛፉ፣ አዳምና ሔዋን ምንጊዜም የይሖዋን መመሪያ ማግኘት እንደሚያስፈልጋቸው ይጠቁማል። ከዛፉ መብላታቸው ግን ራሳቸውን መምራት እንደሚፈልጉ የሚያሳይ ነው፤ ይህ ድርጊታቸው በራሳቸውም ሆነ በዘሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያስከትል ነው። አምላክ የሰጣቸውን ትእዛዝ መጣስ የሚያስከትለው ቅጣት የጉዳዩን ክብደት የሚጠቁም ነው።

  • የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | መስከረም 15
    • 7 አምላክ ለአዳም “[መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ] በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ” ብሎት ነበር። አዳም ይህ “ቀን” የ24 ሰዓት ርዝመት እንዳለው አስቦ ይሆናል። በመሆኑም የአምላክን ትእዛዝ ከጣሰ በኋላ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይሖዋ እርምጃ እንደሚወስድበት ጠብቆ ሊሆን ይችላል። “ቀኑ መሸትሸት ሲል” ይሖዋ አዳምና ሔዋንን አነጋገራቸው። (ዘፍ. 3:8) በዚህ ጊዜ ችሎት የተሰየመ ያህል ነበር፤ አምላክ ጻድቅ ፈራጅ እንደመሆኑ መጠን መጀመሪያ አዳምና ሔዋን የሰጡትን ምላሽ አዳመጠ። (ዘፍ. 3:9-13) ከዚያም በኃጢአተኞቹ ላይ ፍርድ አስተላለፈ። (ዘፍ. 3:14-19) ይሖዋ፣ አዳምንና ሔዋንን ወዲያውኑ ቢያጠፋቸው ኖሮ ከሰው ልጆች ጋር በተያያዘ ያለው ዓላማ አይፈጸምም ነበር። (ኢሳ. 55:11) በሞት እንደሚቀጡ የነገራቸው ሲሆን ኃጢአት ወዲያውኑ በእነሱ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ጀመረ፤ ያም ቢሆን ይሖዋ ከሚያደርጋቸው ሌሎች ዝግጅቶች የሚጠቀሙ ልጆች እንዲወልዱ ፈቀደላቸው። ከአምላክ አመለካከት አንጻር አዳምና ሔዋን የሞቱት ኃጢአት በሠሩበት ቀን ነው፤ ደግሞም በእሱ ፊት አንድ “ቀን” እንደ 1,000 ዓመት ስለሆነ በዚያው ዕለት ሞተዋል ማለት ይቻላል።—2 ጴጥ. 3:8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ