-
ከመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ባልና ሚስት መማር እንችላለንመጠበቂያ ግንብ—2000 | ኅዳር 15
-
-
አምላክ ፕላኔቷ ምድርን በጥሞና ተመለከተ። ምድርን ለሰው ልጆች መኖሪያነት እያዘጋጀ ነበር። ሥራው ሁሉ መልካም መሆኑን አየ። እንዲያውም ሥራው ሲጠናቀቅ “እጅግ መልካም” መሆኑን ገልጿል። (ዘፍጥረት 1:12, 18, 21, 25, 31) ሆኖም አምላክ እዚህ ፍጹም ድምዳሜ ላይ ከመድረሱ በፊት ‘መልካም ስላልሆነ’ አንድ ነገር ተናግሯል። እርግጥ ነው፣ አምላክ እንከን ያለው ነገር አልሠራም። ጉዳዩ የፍጥረት ሥራው ገና ያልተጠናቀቀ መሆኑ ብቻ ነው። ይሖዋ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት” ብሏል።—ዘፍጥረት 2:18
-
-
ከመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ባልና ሚስት መማር እንችላለንመጠበቂያ ግንብ—2000 | ኅዳር 15
-
-
ሰው “ረዳት” ያስፈልገው ነበር። አሁን ምቹ የሆነች ረዳት አገኘ። ሔዋን ገነት የሆነውን ቤታቸውንና እንስሳቱን በመንከባከብ፣ ልጆች በመውለድ እንዲሁም ከእውነተኛ ወዳጅ የሚገኘውን ሐሳብና ድጋፍ በመስጠት ረገድ ለአዳም ፍጹም ተስማሚ ማሟያ ነበረች።—ዘፍጥረት 1:26-30
-