የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክፋት እስከ ዛሬ ያልተወገደው ለምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | መስከረም 15
    • መጽሐፍ ቅዱስ በወቅቱ ምን እንደተፈጠረ ይነግረናል? ሰይጣን ዲያብሎስ በአንድ እባብ በመጠቀም ሔዋንን “በእርግጥ እግዚአብሔር፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሎአልን?” ሲል ጠየቃት። ሔዋን፣ አምላክ የሰጣቸውን ትእዛዝ በነገረችው ጊዜ ሰይጣን እንዲህ አላት:- “መሞት እንኳ አትሞቱም፤ ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው።” ከዚያም ሔዋን የዛፉ ፍሬ የሚጓጓ ሆኖ ስለታያት “ከፍሬው ወስዳ በላች።” አክሎም ዘገባው “ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ” ይላል። (ዘፍጥረት 3:1-6) በመሆኑም አዳምና ሔዋን የተሰጣቸውን የመምረጥ ነፃነት በአግባቡ ሳይጠቀሙበት ቀሩ እንዲሁም አምላክን ባለመታዘዝ ኃጢአት ሠሩ።

      የተፈጸመው ሁኔታ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ተገንዝበሃል? ዲያብሎስ የተናገረው ነገር አምላክ ለአዳም ከሰጠው ትእዛዝ ጋር ይቃረናል። ሰይጣን አዳምና ሔዋን ክፉና መልካሙን ለመወሰን የይሖዋ እርዳታ እንደማያስፈልጋቸው በተዘዋዋሪ መንገድ ተናግሯል። በመሆኑም የሰይጣን ግድድር ይሖዋ ባለው የሰው ልጆችን የመግዛት ሕጋዊ መብት ላይ ጥያቄ አስነስቷል። በዚህም የተነሳ ሰይጣን ያስነሳው እጅግ ወሳኝ ጥያቄ ‘ይሖዋ የሰው ልጆችን የመግዛት መብት አለው?’ የሚለው ነው። ታዲያ እውነተኛው አምላክ ለዚህ ግድድር ምን ምላሽ ይሰጥ ይሆን?

  • ክፋት እስከ ዛሬ ያልተወገደው ለምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | መስከረም 15
    • ሰይጣን በአምላክ የመግዛት መብት ላይ ጥያቄ ካስነሳ ወደ 6,000 የሚጠጉ ዓመታት አልፈዋል። ታዲያ ታሪክ ምን አሳይቷል? ሰይጣን በአምላክ ላይ ያስነሳው ክስ ያሉትን ሁለት ገጽታዎች ተመልከት። ሰይጣን ለሔዋን “መሞት እንኳ አትሞቱም” በማለት ያለ አንዳች ኃፍረት ተናግሯል። (ዘፍጥረት 3:4) ይህ ፍጡር አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ቢበሉ እንደማይሞቱ ሲናገር ይሖዋን ሐሰተኛ ነው ማለቱ ነው። ይህ በእርግጥ ከባድ ክስ ነው! አምላክ በዚህ ረገድ እውነተኛ አይደለም ከተባለ በሌሎች ነገሮች ላይስ እንዴት እምነት ሊጣልበት ይችላል? ይሁን እንጂ፣ ያለፉት ጊዜያት ምን ያሳያሉ?

      አዳምና ሔዋን ለሕመም፣ ለሥቃይ፣ ለእርጅናና በመጨረሻም ለሞት ተዳርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ “አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ” በማለት ይገልጻል። (ዘፍጥረት 3:19፤ 5:5) ይህ አሳዛኝ ውርስ ለሰው ሁሉ የተዳረሰው ከአዳም ነው። (ሮሜ 5:12) ያለፉት ጊዜያት ሰይጣን “ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት”፣ ይሖዋ ደግሞ “የእውነት አምላክ” መሆኑን አረጋግጠዋል።—ዮሐንስ 8:44፤ መዝሙር 31:5

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ