የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መለኮታዊ ትምህርትና የአጋንንት ትምህርት የሚያደርጉት ውጊያ
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ሚያዝያ 1
    • 6. ሰይጣን የይሖዋን መልካምነትና የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ገዥነት የተገዳደረው እንዴት ነበር?

      6 ነገር ግን ሰይጣን የተናገረው ይህን ብቻ አልነበረም። በመቀጠል “ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ” አለ። በሰይጣን አባባል ለመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የተትረፈረፈ ዝግጅት ያደረገላቸው ይሖዋ አምላክ በጣም ጥሩ የሆነ ነገር ከልክሏቸዋል። እንደ አማልክት እንዳይሆኑ ሊከለክላቸው ፈልጓል። ከዚህም የተነሣ ሰይጣን የአምላክን ጥሩነት ተገዳድሯል። እንዲሁም የራስን ፍላጐት ማሳደድና ሆን ብሎ የአምላክን ሕግ መጣስ ጠቃሚ ነው የሚል ትምህርት አስፋፍቷል። አምላክ ሰይጣን በራሱ ፍጥረት ላይ ያለውን ሉዓላዊ ገዥነት በመገዳደር ሰው በሚያደርገው ነገር ላይ ገደብ የማበጀት መብት የለውም ብሏል።

      7. የአጋንንት ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው መቼ ነበር? የአጋንንት ትምህርቶች በዛሬው ጊዜም ተመሳሳይ የሆኑት እንዴት ነው?

      7 የአጋንንት ትምህርት መሰማት የጀመረው በእነዚህ የሰይጣን ቃላት ነው። ዛሬም ቢሆን እነዚህ ክፉ ትምህርቶች ከሰይጣን አነጋገር ጋር የሚመሳሰሉ አምላክ የለሽ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ያስፋፋሉ። በአሁኑ ጊዜ የሌሎች ዓመፀኛ መናፍስትን ድጋፍ ያገኘው ሰይጣን በኤደን ገነት ውስጥ እንዳደረገው አምላክ የሰዎችን አካሄድ የሚገዙ ደንቦችን ለማውጣት ያለውን መብት አሁንም መገዳደሩን አላቆመም። አሁንም እንኳ ቢሆን የይሖዋን ሉዓላዊ ገዥነት ይገዳደራል፤ ሰዎችም ሰማያዊ አባታቸውን እንዳይታዘዙ ለማድረግ ይሞክራል።—1 ዮሐንስ 3:8, 10

  • መለኮታዊ ትምህርትና የአጋንንት ትምህርት የሚያደርጉት ውጊያ
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ሚያዝያ 1
    • 13. ከኤደን ጀምሮ ሰይጣን ለሰው ልጆች ምን ውሸት ሲነግራቸው ቆይቷል?

      13 ሰይጣን ይሖዋን ሐሰተኛ ነው ብሎ በሔዋን ፊት ከሰሰው። በተጨማሪም ፈጣሪያቸውን ካልታዘዙ ሰዎች አማልክት ይሆናሉ በማለት ነገራት። የሰው ልጆች የወደቁበት ዛሬ የምናየው የኃጢአተኝነት ሁኔታ ውሸታሙ ሰይጣን እንጂ ይሖዋ አለመሆኑን አረጋግጧል። ዛሬ እንደምናየው ሰዎች አማልክት አይደሉም! ይሁን እንጂ ሰይጣን በዚያ የመጀመሪያ ውሸት ላይ ሌሎች ተመሳሳይ ውሸቶች መናገሩን ቀጠለ። የሰው ነፍስ የማትሞት ናት የሚል ሐሳብ አመነጨ። በዚህ ሁኔታ በሌላ መንገድ አማልክት መሆን ይቻላል የሚል ማራኪ ሐሳብ ለሰው ልጆች አቀረበ። ከዚያም በዚህ የሐሰት መሠረተ ትምህርት ላይ በመመሥረት የእሳታማ ሲኦልን፣ የመንጽሔን፣ የመናፍስትነትንና የአያቶችን አምልኮ ትምህርቶች አስፋፋ። እነዚህ ውሸቶች አሁንም በመቶ ሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ባሪያ አድርገው ይዘዋል።—ዘዳግም 18:9–13

  • መለኮታዊ ትምህርትና የአጋንንት ትምህርት የሚያደርጉት ውጊያ
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ሚያዝያ 1
    • 16. ሰዎች የራሳቸውን ጥበብ ሲከተሉ የኋላ ኋላ የሚከተሉት ውጤቶች ምንድን ናቸው?

      16 ሰይጣን በኤደን ገነት በተናገረው ውሸት አዳምንና ሔዋንን አምላክ ሳያስፈልጋቸው ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩና በራሳቸው ጥበብ ተማምነው እንዲመሩ አበረታታቸው። ዛሬ፣ የዚህን ውጤት በወንጀሉ፣ በኢኮኖሚው ድቀት፣ በጦርነቶችና በዓለም ላይ በሚገኘው ከፍተኛ መበላለጥ እያየነው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና” ማለቱ አያስደንቅም። (1 ቆሮንቶስ 3:19) ይሁን እንጂ ብዙዎቹ ሰዎች የይሖዋን ትምህርቶች ከመስማት ይልቅ እየተሠቃዩ መኖርን በሞኝነት ይመርጣሉ። (መዝሙር 14:1–3፤ 107:17) መለኮታዊ ትምህርትን የተቀበሉ ክርስቲያኖች ግን በዚህ ወጥመድ ከመያዝ ይድናሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ