-
“ጽናት ሥራውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽም”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሚያዝያ
-
-
12. ኤደንን እንዲጠብቁ ከተመደቡት ኪሩቤል ምን ትምህርት እናገኛለን?
12 ኪሩቤል። ለሰዎች ከተገለጡት መንፈሳዊ ፍጥረታት መካከል የመጀመሪያዎቹ የተዉት ምሳሌ፣ አስቸጋሪ የሆነ ምድብ ሲሰጠን መጽናትን ያስተምረናል። ይሖዋ አምላክ “ወደ ሕይወት ዛፍ [የሚወስደውን] መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ።”[2] (ዘፍ. 3:24) ኪሩቤል የተፈጠሩት ይህን ሥራ እንዲሠሩ እንዳልሆነ የታወቀ ነው! ደግሞም ይሖዋ ለሰው ልጆች በነበረው ዓላማ ውስጥ ኃጢአትና ዓመፅ ቦታ አልነበራቸውም። ያም ሆኖ ትልቅ ቦታ ያላቸው እነዚህ መንፈሳዊ ፍጥረታት፣ የተሰጣቸው ሥራ ለእነሱ የማይመጥን እንደሆነ በመግለጽ ቅሬታቸውን እንዳሰሙ የሚገልጽ ሐሳብ የትም ቦታ አናገኝም። ይህ ምድብ ሰልችቷቸው አልተዉትም። ከዚህ ይልቅ ታዛዥ በመሆን ምድባቸው ላይ ቆይተዋል፤ ምናልባትም ከ1,600 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ የጥፋት ውኃ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ሥራቸውን በጽናት አከናውነዋል!
-
-
“ጽናት ሥራውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽም”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሚያዝያ
-
-
^ [2] (አንቀጽ 12) መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ሥራ የተመደቡት ኪሩቤል ምን ያህል እንደነበሩ የሚናገረው ነገር የለም።
-