የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ቢሞትም እንኳ . . . አሁንም ይናገራል”
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ጥር 1
    • ከሆነ በጣም ተሳስታለች። እሷና አዳም፣ ቃየንን ሲያሳድጉ እንዲህ ያሉ ሐሳቦችን ነግረውት ከሆነ ይህ፣ ልጃቸው ፍጽምና የጎደለው መሆኑ ከሚያሳድርበት ተጽዕኖ ጋር ተዳምሮ ትዕቢተኛ እንዲሆን አድርጎት መሆን አለበት። ከጊዜ በኋላ ሔዋን ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ይሁንና ከእሱ ጋር በተያያዘ ለቃየን እንደተናገረችው ያለ የኩራት ሐሳብ አልተናገረችም። ሁለተኛ ልጃቸውን አቤል ብለው የሰየሙት ሲሆን ትርጉሙም “ተን” ወይም “ባዶ” ማለት ሊሆን ይችላል። (ዘፍጥረት 4:2) ልጃቸውን እንዲህ ብለው መሰየማቸው የቃየንን ያህል ከአቤል ትልቅ ነገር እንደማይጠብቁ የሚጠቁም ይሆን? በእርግጠኝነት መናገር አንችልም።

  • “ቢሞትም እንኳ . . . አሁንም ይናገራል”
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ጥር 1
    • ሁለቱ ወንዶች ልጆች እያደጉ ሲሄዱ አዳም፣ ቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ለማቅረብ የሚያስችሉ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ሳያሠለጥናቸው አልቀረም። ቃየን ገበሬ ሲሆን አቤል ደግሞ በግ ጠባቂ ሆነ።

  • “ቢሞትም እንኳ . . . አሁንም ይናገራል”
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ጥር 1
    • አቤል ጊዜ ወስዶ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ያሰላስል እንደነበረ ጥርጥር የለውም። አቤል መንጋውን ሲንከባከብ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። አንድ እረኛ ሥራውን ለማከናወን ብዙ መጓዝ ነበረበት። ለእነዚህ ገራም ፍጥረታት ለምለም ሣር፣ ምርጥ የውኃ ጉድጓድ እንዲሁም ከሁሉ የተሻለ መጠለያ ያለው ማረፊያ ቦታ ለማግኘት ሲል ኮረብቶችን እየወጣና እየወረደ፣ ሸለቆዎችን እያቋረጠና ወንዞችን እየተሻገረ ይጓዝ ነበር። ከአምላክ ፍጥረታት ሁሉ በጎች በቀላሉ ሊጠቁ ስለሚችሉ የሰው ልጅ እንዲመራቸውና ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ታስበው የተፈጠሩ ይመስላሉ። አቤል፣ እሱም ቢሆን ከማንኛውም ሰው በላይ ጥበበኛና ኃያል ከሆነ አካል አመራር፣ ጥበቃና እንክብካቤ ማግኘት እንደሚያስፈልገው አስተውሎ ይሆን? አቤል በዚህ ረገድ ስሜቱን በጸሎት ይገልጽ እንደነበረና ይህም እምነቱን እንዳጠናከረለት ጥርጥር የለውም።

      አቤል የፍጥረት ሥራዎችን መመልከቱ አፍቃሪ በሆነው ፈጣሪው ላይ እምነት ለማዳበር ጠንካራ መሠረት ሆኖለታል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ