የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቃየንና አቤል በጉልምስና ዕድሜያቸው ሳይሆን አይቀርም ለይሖዋ መሥዋዕት አቀረቡ። አቤል እረኛ እንደመሆኑ መጠን “ከበጎቹ በኩራትና ከስቡ” መሥዋዕት ማቅረቡ አያስደንቅም። በአንጻሩ ደግሞ ቃየን “ከምድር ፍሬ” አቀረበ። ይሖዋ የአቤልን መሥዋዕት ሲቀበል “ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም።” (ዘፍጥረት 4:​3-5) ለምን?

      አንዳንዶች የአቤል መሥዋዕት “ከበጎቹ በኩራት” የቀረበ ሲሆን የቃየን ግን እንደነገሩ “ከምድር ፍሬ” በመቅረቡ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም ዘገባው ይሖዋ “ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ” በደስታ ሲመለከት “ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ” ግን በደስታ አለመመልከቱን ስለሚገልጽ ችግሩ ያለው ቃየን ባቀረበው ነገር ጥራት ላይ አልነበረም። ስለዚህ ይሖዋ በአንደኛ ደረጃ የተመለከተው የአምላኪውን የልብ ዝንባሌ ነበር። እንዲህ ሲያደርግ የተመለከተው ነገር ምን ነበር? ዕብራውያን 11:​4 አቤል መሥዋዕቱን ያቀረበው “በእምነት” መሆኑን ይናገራል። ስለዚህ ቃየን የአቤል መሥዋዕት ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስቻለው እምነት ይጎድለው እንደነበር ግልጽ ነው።

      በዚህ ረገድ የአቤል መሥዋዕት ደም ማፍሰስን ማካተቱ ትኩረት የሚስብ ነው። አምላክ ተረከዙ ላይ ስለሚነከሰው ዘር ከገባው ቃል በመነሳት ጉዳዩ አንድ ሕይወት መሥዋዕት እንዲሆን ይጠይቃል የሚል ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ ሳያደርሰው አይቀርም። ስለዚህ የአቤል መሥዋዕት ለዕርቅ የቀረበ ልመና ሊሆን ይችላል። እንዲሁም መሥዋዕቱ አምላክ በወሰነው ጊዜ ለኃጢአት ማስተሰሪያ የሚሆን ተመጣጣኝ ቤዛ እንደሚያቀርብ እምነት እንዳለው ያሳያል።

  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ የአቤልን መሥዋዕት መቀበሉን ያሳየው እንዴት እንደሆነ አይገልጽልንም። አንዳንዶች ከሰማይ የወረደ እሳት መሥዋዕቱን እንደበላው ይናገራሉ። ያም ሆነ ይህ ቃየን መሥዋዕቱ ተቀባይነት እንዳላገኘ ሲገነዘብ ‘እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።’ (ዘፍጥረት 4:​5) ቃየን ወደ ጥፋት እያመራ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ