የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቃየንና አቤል በጉልምስና ዕድሜያቸው ሳይሆን አይቀርም ለይሖዋ መሥዋዕት አቀረቡ። አቤል እረኛ እንደመሆኑ መጠን “ከበጎቹ በኩራትና ከስቡ” መሥዋዕት ማቅረቡ አያስደንቅም። በአንጻሩ ደግሞ ቃየን “ከምድር ፍሬ” አቀረበ። ይሖዋ የአቤልን መሥዋዕት ሲቀበል “ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም።” (ዘፍጥረት 4:​3-5) ለምን?

      አንዳንዶች የአቤል መሥዋዕት “ከበጎቹ በኩራት” የቀረበ ሲሆን የቃየን ግን እንደነገሩ “ከምድር ፍሬ” በመቅረቡ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም ዘገባው ይሖዋ “ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ” በደስታ ሲመለከት “ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ” ግን በደስታ አለመመልከቱን ስለሚገልጽ ችግሩ ያለው ቃየን ባቀረበው ነገር ጥራት ላይ አልነበረም። ስለዚህ ይሖዋ በአንደኛ ደረጃ የተመለከተው የአምላኪውን የልብ ዝንባሌ ነበር። እንዲህ ሲያደርግ የተመለከተው ነገር ምን ነበር? ዕብራውያን 11:​4 አቤል መሥዋዕቱን ያቀረበው “በእምነት” መሆኑን ይናገራል። ስለዚህ ቃየን የአቤል መሥዋዕት ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስቻለው እምነት ይጎድለው እንደነበር ግልጽ ነው።

  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • በአንፃሩ ደግሞ ቃየን ስለሚያቀርበው መሥዋዕት ብዙም ትኩረት ሳይሰጥ እንዲሁ ለታይታ ያደረገው ይመስላል። አንድ የ19ኛው መቶ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ “እርሱ መሥዋዕቱን ያቀረበው እንዲያው ለይሉኝታ ሲል ብቻ ነው ለማለት ይቻላል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። “ያቀረበው መሥዋዕት በእርሱና በፈጣሪው መካከል ያለውን ዝምድና የሚያሻክር ነገር መኖሩንና ለኃጢአት ንስሐ የመግባትንም ሆነ የስርየትን አስፈላጊነት አለመገንዘቡን በግልጽ ያሳይ ነበር።”

      ከዚህ በተጨማሪም ቃየን በኩር እንደመሆኑ መጠን እባቡን ማለትም ሰይጣንን የሚያጠፋው ተስፋ የተደረገበት ዘር እርሱ እንደሆነ አድርጎ በትዕቢት ሳያስብ አይቀርም። ሔዋንም ሳትቀር ለበኩር ልጅዋ ይህ ዓይነቱን ጉጉት የታከለበት ምኞት አሳድራ ሊሆን ይችላል። (ዘፍጥረት 4:​1) እርግጥ ነው፣ ቃየንም ሆነ ሔዋን እንዲህ ዓይነት ምኞት ከነበራቸው በጣም ተሳስተዋል።

      መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ የአቤልን መሥዋዕት መቀበሉን ያሳየው እንዴት እንደሆነ አይገልጽልንም። አንዳንዶች ከሰማይ የወረደ እሳት መሥዋዕቱን እንደበላው ይናገራሉ። ያም ሆነ ይህ ቃየን መሥዋዕቱ ተቀባይነት እንዳላገኘ ሲገነዘብ ‘እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።’ (ዘፍጥረት 4:​5) ቃየን ወደ ጥፋት እያመራ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ