የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • ቃየን ስሜቱን እንዲመረምር ይሖዋ ሊረዳው ሞክሯል። “ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ?” ሲል ጠየቀው። ቃየን የቀረበለት ጥያቄ ስሜቱንና ግፊቱን እንዲመረምር በቂ አጋጣሚ ሰጥቶታል። በመቀጠልም ይሖዋ “መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፣ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት” አለው።​—⁠ዘፍጥረት 4:​6, 7 (በገጽ 23 ላይ ያለውን ሣጥን ተመልከት።)

  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • ቃየን አቤልን ከመግደሉ በፊትም ሆነ ከገደለው በኋላ ‘መልካም ለማድረግ’ ፈቃደኛ አልሆነም። በእርሱ ላይ ኃጢአት እንዲነግሥ መረጠ። በዚህ ምክንያት ቃየን ሰብዓዊው ቤተሰብ ከሚኖርበት አካባቢ ተባረረ። በአቤል ሞት ምክንያት ማንም ሰው ቃየንን እንዳይበቀለው “ምልክት” ተደረገ፤ ይህ ምልክት የተባለው ነገር ቃየን አንዳይገደል የሚደነግግ ሕግ ሊሆን ይችላል።​—⁠ዘፍጥረት 4:​15

  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 1
    • “ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ?” ይሖዋ እነዚህን ጥያቄዎች በመጠየቅ ቃየን ጉዳዩን እንዲያስብበት በደግነት ሊረዳው ሞክሯል። ቃየን የመምረጥ ነፃነት ያለው ፍጡር ስለሆነ ይሖዋ አካሄዱን እንዲለውጥ አላስገደደውም። (ከዘዳግም 30:​19 ጋር አወዳድር።) የሆነ ሆኖ ይሖዋ፣ ቃየን የተከተለው አጓጉል አካሄድ ሊያስከትልበት የሚችለውን መዘዝ ከመንገር ወደኋላ አላለም። ቃየንን “መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው” ሲል አስጠንቅቆታል።​—⁠ዘፍጥረት 4:​6, 7

      ይሖዋ ይህን የመሰለ ጠንካራ ተግሣጽ ቢሰጠውም እንኳ ቃየንን ‘ምንም ተስፋ እንደሌለው’ አድርጎ እንዳልተመለከተው ልብ ማለት ያስፈልጋል። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ፣ ቃየን አካሄዱን ካስተካከለ የሚያገኛቸውን በረከቶች ከመንገሩም በላይ ከፈለገ ይህን ችግር ማሸነፍ እንደሚችል ያለውን ትምክህት ገልጿል። ይሖዋ “መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን?” ሲል ነግሮታል። በተጨማሪም ወደ ግድያ ሊያመራው የሚችለውን ቁጣ በተመለከተ “አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት” ብሎታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ