የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የኖኅ መርከብ እና የመርከብ ምህንድስና
    ንቁ!—2007 | ጥር
    • የዘፍጥረት ዘገባ አምላክ ምድርን ከክፋት ለማጽዳት በውኃ እንዳጥለቀለቃት ይናገራል። አምላክ ኖኅ ራሱን፣ ቤተሰቡንና የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎችን ከዚህ የጥፋት ውኃ ለማዳን መርከብ እንዲሠራ ትእዛዝ ሰጠው። ኖኅ የሚሠራት መርከብ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13.5 ሜትር መሆን እንዳለበት ነገረው። (ዘፍጥረት 6:15) የዚህች ግዙፍ መርከብ መጠን በግምት 40,000 ሜትር ኩብ የሚያክል ሲሆን የቅንጦት መርከብ ከነበረችው ከታይታኒክ ጋር ተመጣጣኝ ነው።

  • የኖኅ መርከብ እና የመርከብ ምህንድስና
    ንቁ!—2007 | ጥር
    • መርከቧ የነበራት ነፋስና ሞገድን የመቋቋም ችሎታ

      የመርከቧ ርዝመት ወርዷን ስድስት እጥፍ እንዲሁም ቁመቷን አሥር እጥፍ ይበልጣል። በዘመናችን የሚሠሩ ብዙ መርከቦች ርዝመት፣ ወርድና ቁመት ከዚህ ጋር ተመጣጣኝ ነው። እርግጥ እነዚህ መርከቦች ርዝመታቸው ከወርዳቸው ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን የሚደረገው ውኃውን ሰንጥቀው እንዲሄዱ ከሚያስችላቸው ኃይል ጋር በተያያዘ ነው። የኖኅ መርከብ ግን የተሠራችው በውኃ ላይ እንድትንሳፈፍ ብቻ ነው። ሆኖም ይህን ዓላማዋን ምን ያህል በብቃት ተወጥታለች?

      መርከቦች በባሕር ላይ ሲጓዙ የሚያጋጥማቸው ነፋስና ሞገድ የማይበግራቸው ከሆኑ ጥሩ የመቋቋም ችሎታ (seakeeping behavior) እንዳላቸው ተደርጎ ይታሰባል። ይህም ቢሆን የመርከቦቹ ርዝመት፣ ወርድና ቁመት ተመጣጣኝ በመሆኑ ላይ በእጅጉ የተመካ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ታላቅ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት የውኃ መጥለቅለቅ እንደተከሰተ እንዲሁም አምላክ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ነፋስ እንዲነፍስ እንዳደረገ ይናገራል። (ዘፍጥረት 7:11, 12, 17-20፤ 8:1) ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ነፋሱ ወይም ሞገዱ ምን ያህል ከባድ እንደነበረ ባይናገርም በዛሬውም ጊዜ እንደሚታየው ሁሉ ነፋሱም ሆነ ሞገዱ ኃይለኛና ተለዋዋጭ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ነፋሱ ረዘም ላለ ጊዜ በኃይል በነፈሰ መጠን ሞገዱም የዚያኑ ያህል በጣም ወደ ላይ እንዲነሳ ያደርገዋል። በተጨማሪም ማንኛውም ዓይነት የመሬት ነውጥ ከባድ ሞገድ እንዲነሳ ምክንያት ይሆናል።

      መርከቧ ተመጣጣኝ ተደርጋ መሠራቷ ከመጠን በላይ እንዳትዋልል ከመርዳቱም ሌላ ከመገልበጥ አድኗታል። እንዲሁም መርከቧ የተሠራችው እንድትዋልል የሚያደርጋትን ግፊት መቋቋም እንድትችል ተደርጋ ነው። ሞገዱ መርከቧን በአንደኛው ጫፍ በተደጋጋሚ ጊዜያት ወደ ላይ ወደ ታች የሚያደርጋት በመሆኑ ምክንያት ከመጠን በላይ መዋለሏ በውስጧ የተሳፈሩትን ሰዎችም ሆነ እንስሳት እንዲንገላቱ ያደርጋቸዋል። ከዚህም በላይ ይህ ግፊት በመርከቧ ላይ ከባድ ጫና ይፈጥራል። የተዋቀረችበት መንገድ ኃይለኛ ሞገድ መርከቧን በአንድ ጊዜ ከፊትና ከኋላ ወደ ላይ ቢያነሳት መሃል ለመሃል ልምጥ እንድትል የሚያደርጋትን ኃይል መቋቋም የሚያስችል መሆን አለበት። ያም ሆኖ ግን ከባድ ሞገድ መርከቧን መሃል ለመሃል ወደ ላይ ካነሳት ከፊትና ከኋላ ምንም የሚደግፋት ነገር ስለማይኖር ወደ ላይ ልምጥ ልትል ትችላለች። ስለዚህ አምላክ ለኖኅ የመርከቧን ርዝመት ከቁመቷ በአሥር እጅ አስበልጦ እንዲሠራት አዘዘው። አሁን ያሉት የመርከብ ሠራተኞች በመርከብ ላይ የሚደርሰውን እንዲህ ያለውን ጫና ለመቋቋም በዚህ ሬሾ መርከብ መገንባት ጠቃሚ መሆኑን የተረዱት ብዙ ችግር ካሳለፉ በኋላ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ