-
ኖኅ ካሰፈረው የግል ማስታወሻ ምን ትምህርት እናገኛለን?መጠበቂያ ግንብ—2003 | ግንቦት 15
-
-
አሁን ደግሞ ዘፍጥረት 8:5-17ን እናንብብ። የተራሮቹ ራሶች ከሁለት ወር ተኩል (73 ቀናት) ገደማ በኋላ ማለትም “በአሥረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን” ተገለጡ። (ዘፍጥረት 8:5)b ከሦስት ወር (90 ቀናት) በኋላ ማለትም “በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን” ወይም መስከረም 2369 አጋማሽ ላይ ኖኅ የመርከቡን ክዳን አነሣ። “ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ።” (ዘፍጥረት 8:13) አንድ ወር ከ27 ቀን (57 ቀናት) በኋላ “በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛው ቀን [ኅዳር 2369 ከዘአበ አጋማሽ ላይ] ምድር ደረቀች።” በዚህ ጊዜ ኖኅና ቤተሰቡ ከመርከቡ ወጡ። ስለዚህ ኖኅና ቤተሰቡ መርከቡ ውስጥ የቆዩት አንድ የጨረቃ ዓመት ከአሥር ቀን (370 ቀናት) ነው።—ዘፍጥረት 8:14
-
-
ኖኅ ካሰፈረው የግል ማስታወሻ ምን ትምህርት እናገኛለን?መጠበቂያ ግንብ—2003 | ግንቦት 15
-
-
b ካይል ዴልች ኮሜንታሪ ኦን ዚ ኦልድ ቴስታመንት የተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 148 እንዲህ ይላል:- “የተራሮቹ ራሶች ማለትም መርከቧ ያረፈችባቸው የአርሜንያ ተራራማ አካባቢዎች የተገለጡት ምናልባት መርከቧ ካረፈች ከ73 ቀናት በኋላ ሊሆን ይችላል።”
-