የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ ‘ከወዳጁ’ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን በብዙ ሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ጠቃሚ ሆኖአል
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 3, 4. (ሀ) አብርሃም በእርሱ ላይ የነበረውን እምነትና ትምክህት ይሖዋ ከፍ አድርጎ እንደተመለከተው የሚያሳየው ምንድን ነው? (ለ) ይሖዋ በኢሳይያስ 41:8 ላይ ያለውን ቃሉን ወደ ከፍተኛው ፍጻሜ ያደረሰው እንዴት ባለ አነጋገር ነው?

      3 ይህ የእምነትና የተግባር ሰው ከከለዳውያን ከተማ ከዑር የመጣና ዕብራዊ ተብሎ በመጠራት የመጀመሪያው የሆነ ሰው ነው። (ዘፍጥረት 14:13) ይህ ስያሜ የእስራኤል ሕዝብ ለሆኑት ዘሮቹም የሚሠራ ሆኗል። (ፊልጵስዩስ 3:5) ይሖዋ አምላክ አብርሃምን ወዳጁ በማድረጉ ምስጢራዊ ወደሆኑ ጉዳዮቹም ጭምር አስገብቶት ነበር። በዘፍጥረት 18:17–19 ላይ የሰፈረው ሐሳብ ይህንን ያመለክታል።

  • አምላክ ‘ከወዳጁ’ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን በብዙ ሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ጠቃሚ ሆኖአል
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 6 ኤፍራጥስ አብርሃምና ቤተሰቡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ተሻግረው ያለፉት ወንዝ ነው። ወንዙን በተሻገሩበት ጊዜ እርሱ 75 ዓመት ቢሆነውና ሚስቱም ልጅ የመውለጃዋ ጊዜ ቢያልፍም እንኳ አብርሃም ልጅ አልነበረውም። (ዘፍጥረት 12:1–5) ሆኖም እንደነዚህ ባሉ ተቃራኒ ሁኔታዎች ውስጥ እያለ አምላክ ለታዛዡ ለአብርሃም:- “ወደ ሰማይ ተመልከት፣ ከዋክብትንም ልትቆጥራቸው ትችል እንደሆነ ቁጠር . . . ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።”— ዘፍጥረት 15:2–5

      7. (ሀ) ቃል ኪዳኑ ምን ተብሎ ይጠራል? (ለ) የጸናው በየትኛው ዓመት ላይ ነው? በአብርሃም ሕይወት ምን በሆነበት ወቅት ላይ ነበር? (ሐ) ይህ የሆነው ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የሕግ ቃል ኪዳን ከመደረጉ ከስንት ዓመታት በፊት ነው?

      7 ይሖዋ ‘ከወዳጁ’ ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን የአብርሃም ቃል ኪዳን ብለን እንጠራዋለን። ይህ ቃል ኪዳን የጸናው አብርሃም የአምላክን የቃል ኪዳን ብቃቶች በማሟላት ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲጓዝ የኤፍራጥስን ወንዝ ከተሻገረበት ጊዜ ይኸውም ከ1943 ከዘአበ ጀምሮ ነው። በዚያ ዓመት ይሖዋ አምላክ ልጅ የሌለውን አብርሃምን “ዘር” ሰጥቶ ለመባረክ ግዴታ ውስጥ ገባ። በሲና ተራራ ላይ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የተደረገው ቃል ኪዳን ክፍል የሆነው ሕግ የተሰጠው ከዚያ 430 ዓመት ቆይቶ በ1513 ከዘአበ ነው።— ዘፍጥረት 12:1–7፤ ዘፀአት 24:3–8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ