የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአብርሃም ዓይነት እምነት ይኑራችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ነሐሴ 15
    • 10. በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ምን ችግር ተፈጠረ? ችግሩ በፍጥነት እልባት ማግኘት የነበረበት ለምንድን ነው?

      10 “ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው። በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም የነበራቸው እጅግ ነበረና በአንድነት ሊቀመጡ አልቻሉም። የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ በዚያም ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።” (ዘፍጥረት 13:5-7) ምድሪቱ የአብራምንና የሎጥን መንጎች ለመመገብ የሚያስችል በቂ ውኃና ግጦሽ አልነበራትም። በዚህም የተነሳ በእረኞቹ መካከል ጠብና ጭቅጭቅ ተፈጠረ። በእውነተኛ የአምላክ አምላኪዎች መካከል እንዲህ ያለው ጥል ሊፈጠር አይገባም። የተፈጠረው ጭቅጭቅ እልባት ካላገኘ እየከረረ ሊሄድ ይችላል። ታዲያ አብራም ጉዳዩን እንዴት ይወጣው ይሆን? ሎጥን አባቱ ከሞተበት በኋላ እንደ ልጁ አድርጎ ያሳደገው እርሱ ነው። አብራም በዕድሜ ታላቅ እንደመሆኑ መጠን የተሻለውን የመውሰድ መብት አልነበረውም?

      11, 12. አብራም ለሎጥ ምን ደግነት የተሞላበት ግብዣ አቀረበለት? ሎጥ ያደረገው ምርጫ ጥበብ የጎደለው የነበረው እንዴት ነው?

      11 ሆኖም “አብራምም ሎጥን አለው:- እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።” ከቤቴል አቅራቢያ “በጳለስጢና ካሉት አካባቢውን ለመቃኘት ከሚያስችሉ ከፍታዎች የተሻለ ነው” የተባለለት ቦታ አለ። ምናልባት ከዚህ ሳይሆን አይቀርም “ሎጥም ዓይኑን አነሣ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ዞዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።”​—⁠ዘፍጥረት 13:8-10

  • የአብርሃም ዓይነት እምነት ይኑራችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ነሐሴ 15
    • 13. ገንዘብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ውዝግብ ውስጥ ለገቡ ክርስቲያኖች የአብራም ምሳሌ ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?

      13 አብራም ከጊዜ በኋላ ዘሮቹ መላውን ምድር እንደሚወርሱ ይሖዋ በገባለት ቃል ላይ እምነት ያሳደረ ቢሆንም እንኳ በአንዲት ቁራሽ መሬት ለመጨቃጨቅ አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ ከጊዜ በኋላ በ1 ቆሮንቶስ 10:​24 ላይ “እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ” ከሚለው መሠረታዊ ሥርዓት ጋር በሚስማማ መንገድ ተመላልሷል። ገንዘብን በተመለከተ ከእምነት ባልንጀራቸው ጋር መግባባት ላልቻሉ ይህ ጥሩ ማሳሰቢያ ነው። አንዳንዶች ማቴዎስ 18:​15-17 ላይ የሚገኘውን ምክር ከመከተል ይልቅ ወንድሞቻቸውን ፍርድ ቤት ከስሰዋቸዋል። (1 ቆ⁠ሮ​ንቶስ 6:1, 7) በይሖዋ ስም ላይ ነቀፋ ከማምጣት ወይም የክርስቲያን ጉባኤን ሰላም ከማወክ ይልቅ ገንዘባችንን ብናጣ የተሻለ እንደሚሆን ከአብራም ምሳሌ እንማራለን።​—⁠ያዕቆብ 3:18

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ