የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ የሰጠውን ተስፋ በመፈጸም ረገድ አይዘገይም
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሰኔ 1
    • መሙላት ያለበት የኃጢአት ጽዋ

      አምላክ በጥንት ጊዜ ከሰው ዘር ጋር የነበረውን ግንኙነት ስንመረምር አብዛኛውን ጊዜ ሰዎቹ ከእንግዲህ ወዲያ ምንም መሻሻል አያደርጉም የሚል መደምደሚያ ላይ እስከሚደርስ ድረስ ፍርዱን ያዘገይ እንደነበር እንመለከታለን። ለምሳሌ ያህል አምላክ በከነዓናውያን ላይ የቅጣት እርምጃ ከመውሰዱ ከረጅም ጊዜ በፊት ስለሠሩት ኃጢአት ለአብርሃም ነግሮት ነበር። ሆኖም ፍርዱን የሚያስፈጽምበት ጊዜ አልደረሰም ነበር። ለምን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “የአሞራውያን [የከነዓናውያን] ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና” ወይም የኖክስ ትርጉም እንደሚለው “የአሞራውያን ክፋት ጽዋ ገና አልሞላም ነበር።”​—⁠ዘፍጥረት 15:​16a

      ይሁን እንጂ ከ400 ዓመታት በኋላ የአምላክ ፍርድ መጣ፤ የአብርሃም ዘሮች የሆኑት እስራኤላውያንም ምድሪቱን ወረሱ። ረዓብንና ገባዖናውያንን የመሳሰሉ ጥቂት ከነዓናውያን በነበራቸው ዝንባሌና በወሰዱት እርምጃ ምክንያት የዳኑ ቢሆንም በዘመናዊ አርኪኦሎጂያዊ ቁፋሮዎች የተገኙ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት አብዛኛው ሕዝብ የረከሰ ተግባር በመፈጸም እጅግ ርቆ ሄዶ ነበር። የወንድ የፆታ ብልት አምልኮ ያካሂዱና በቤተ መቅደስ ውስጥ ግልሙትና ይፈጽሙ የነበረ ሲሆን ልጆቻቸውንም ይሠዉ ነበር። ሃሌይስ ባይብል ሃንድቡክ እንዲህ ይላል:- “የከነዓናውያንን ከተሞች ፍርስራሽ ቆፍረው ጥናት ያደረጉ አርኪኦሎጂስቶች አምላክ ለምን ከዚያ ቀደም ብሎ እንዳላጠፋቸው በጣም ይገርማቸዋል።” በመጨረሻ የከነዓናውያን ‘ኃጢአት ተፈጸመ፤’ የክፋታቸው ‘ጽዋ ሞላ።’ ስለሆነም አምላክ ጥሩ አቋም የነበራቸውን ሰዎች አድኖ ምድሪቱን ከክፋት ማጽዳቱ ፍትሕ የጎደለው እርምጃ ነው ብሎ አምላክን የሚከስ ሊኖር አይችልም።

  • አምላክ የሰጠውን ተስፋ በመፈጸም ረገድ አይዘገይም
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሰኔ 1
    • a ዘ ሶንሲኖ ሹሜሽ በተባለው መጽሐፍ ላይ የዚህ ጥቅስ የግርጌ ማስታወሻ እንዲህ ይላል:- “አምላክ የአንድ ብሔር የኃጢአት ጽዋ እስኪሞላ ድረስ ቅጣቱን ስለማያስፈጽም ሕዝቡ ከምድሪቱ አይባረሩም ነበር።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ