የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ “ልዕልት” ብሎ ጠርቷታል
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 5
    • አብርሃም ብዙ አባላት ካለው ቤተሰቡ ጋር ሆኖ የኤፍራጥስን ወንዝ በመሻገር ወደ ከነአን ምድር ከገባ አሥር ዓመት አልፏል። ሣራ፣ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ዘርና ብሔር ለማስገኘት ይሖዋ ባወጣው ዓላማ ውስጥ ባሏ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ስለተገነዘበች ወደማያውቁት አገር ባደረጉት ጉዞ ባለቤቷን በፈቃደኝነት ደግፋዋለች። ይሁንና ሣራ በዚህ የይሖዋ ዓላማ ውስጥ ምን ድርሻ ይኖራታል? ሣራ መሃን ስትሆን አሁን ደግሞ 75 ዓመት ሆኗታል። በመሆኑም ‘አብርሃም ከእኔ ጋር እየኖረ የይሖዋ ተስፋ ሊፈጸም የሚችለው እንዴት ነው?’ የሚል ሐሳብ መጥቶባት ሊሆን ይችላል። ሣራ ይህ ጉዳይ ቢያሳስባት አልፎ ተርፎም መታገሥ ቢያቅታት አይፈረድባትም።

  • አምላክ “ልዕልት” ብሎ ጠርቷታል
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017 | ቁጥር 5
    • ሣራ ወደ ኋላ ከመመልከት ይልቅ ወደ ፊት ተመልክታለች። በመሆኑም ባሏ በከነአን ምድር ውስጥ በሚያደርገው ጉዞ ደግፋዋለች፤ በየጊዜው ድንኳኖቻቸውን ነቅለውና መንጎቻቸውን ይዘው ሲጓዙ እንዲሁም በሄዱበት ቦታ ድንኳናቸውን እንደ አዲስ ሲተክሉ ታግዘው ነበር። ሣራ ሌሎች ተፈታታኝ ሁኔታዎችንና ለውጦችንም በጽናት አሳልፋለች። ይሖዋ ለአብርሃም ከዚህ በፊት የሰጠውን ተስፋ የደገመለት ቢሆንም ሣራን ግን ምንም አላላትም!—ዘፍጥረት 13:14-17፤ 15:5-7

      በመጨረሻ ሣራ በውስጧ ስታውጠነጥን የቆየችውን ሐሳብ ለአብርሃም ለመናገር ወሰነች። “እንግዲህ እንደምታየው ይሖዋ ልጆች እንዳልወልድ አድርጎኛል” ብላ በምትናገርበት ጊዜ በውስጧ ካለው ስሜት ጋር እየታገለች እንደሆነ ከፊቷ ማየት ይቻላል። ሣራ፣ ከአገልጋይዋ ከአጋር ልጆች እንዲወልድ ባሏን ጠየቀችው። ሣራ ለባሏ ይህን ጥያቄ ማቅረብ ምን ያህል ከብዷት ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ትችላለህ? በዛሬው ጊዜ ለምንኖረው ሰዎች እንዲህ ያለው ጥያቄ እንግዳ ሊሆን ይችላል፤ በዚያ ዘመን ግን አንድ ወንድ ወራሽ የሚሆነው ልጅ ለማግኘት ሲል ሁለተኛ ሚስት ማግባቱ ወይም ቁባት መያዙ ያልተለመደ ነገር አልነበረም።b ሣራ፣ አምላክ ከአብርሃም ዘሮች ብሔር ለማቋቋም ያለው ዓላማ የሚፈጸመው በዚህ መንገድ እንደሆነ አስባ ይሆን? ምን እንዳሰበች ባናውቅም ከባድ መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኛ ነበረች። የአብርሃም ምላሽ ምን ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ፣ አብርሃም “[የሣራን] ቃል ሰማ” ይላል።—ዘፍጥረት 16:1-3

      ዘገባው ሣራ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ እንድታቀርብ ያነሳሳት ይሖዋ እንደሆነ ይገልጻል? በፍጹም። ከዚህ ይልቅ ያቀረበችው ሐሳብ ሰብዓዊ አመለካከት እንደነበራት የሚጠቁም ነው። ልጅ እንዳትወልድ ያደረጋት አምላክ እንደሆነ ተሰምቷት ነበር፤ አምላክ ሌላ መፍትሔ ሊያዘጋጅ እንደሚችል አላሰበችም። ሣራ፣ መፍትሔ ብላ ያቀረበችው ሐሳብ በራሷ ላይ ሐዘንና ችግር የሚያስከትል ነበር። ያም ሆኖ ያቀረበችው ሐሳብ፣ ራስ ወዳድ እንዳልሆነች የሚያሳይ ነው። ከምንም በላይ የራሳቸውን ፍላጎት የሚያስቀድሙ ሰዎች በሞሉበት ዓለም ውስጥ ሣራ ያሳየችው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ መንፈስ የሚያስደንቅ አይደለም? እኛም ከራሳችን ፍላጎት ይልቅ የአምላክን ዓላማዎች ለማስቀደም ፈቃደኞች ከሆንን ሣራን በእምነቷ እየመሰልናት ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ