የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “አዎ፣ እሄዳለሁ”
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 3
    • አንድ ቀን አመሻሹ ላይ እንስራዋን ውኃ ከሞላች በኋላ አንድ አረጋዊ ወደ እሷ እየሮጠ መጥቶ “እባክሽ ከእንስራሽ ውኃ ልጎንጭ” አላት። ሰውየው ቀላል ነገር ነው የጠየቃት፤ ያውም በአክብሮት! ርብቃ፣ ሰውየው ብዙ መንገድ ተጉዞ እንደመጣ መረዳት ችላለች። በመሆኑም እንስራዋን በፍጥነት ከትከሻዋ ላይ አውርዳ እንዲያው ፉት እንዲል ሳይሆን እስኪረካ ድረስ የሚጠጣው ቀዝቀዝ ያለ ንጹሕ ውኃ ሰጠችው። እዚያው አካባቢ በርከክ ያሉ አሥር ግመሎች እንዳሉት ሆኖም እነሱ የሚጠጡት ውኃ ገንዳው ውስጥ አለመሞላቱን አየች። ደግነት የሚንጸባረቅባቸው ዓይኖቹ በትኩረት እንደሚከታተሏት ገብቷታል፤ በመሆኑም አቅሟ በሚፈቅደው መጠን ሰውየውን ልትረዳው ፈልጋለች። ከዚያም “ግመሎችህም ጠጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ውኃ እቀዳላቸዋለሁ” አለችው።—ዘፍጥረት 24:17-19

      ርብቃ ለአሥሩ ግመሎች ውኃ ለመስጠት ሐሳብ ያቀረበችው ጠጥተው እስኪረኩ ድረስ እንጂ እንዲቃመሱ ያህል ብቻ አለመሆኑን ልብ በል። ውኃ የጠማው አንድ ግመል ከ95 ሊትር በላይ ውኃ ሊጠጣ ይችላል! አሥሩም ግመሎች በጣም ጠምቷቸው ከነበረ ርብቃ ብዙ ሰዓት የሚፈጅ አድካሚ ሥራ ይጠብቃታል ማለት ነው። የተፈጸመውን ሁኔታ ስናስብ ግመሎቹ በጣም ተጠምተው ነበር ለማለት አያስደፍርም።a ይሁንና ርብቃ ግመሎቹን ለማጠጣት ሐሳብ ስታቀርብ ይህን ታውቅ ነበር? በጭራሽ። ለአካባቢው ባይተዋር ለሆነው ለዚህ አረጋዊ ሰው፣ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ለማሳየት ስትል ጉልበቷን ሳትቆጥብ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኝነቱም ሆነ ጉጉቱ ነበራት። እሱም በሐሳቧ ተስማማ። ከዚያም እንስራዋን ለመሙላት እየተመላለሰች ገንዳው ውስጥ ውኃ ደጋግማ ስትገለብጥ በመገረም ይመለከታት ነበር።—ዘፍጥረት 24:20, 21

      ርብቃ የአብርሃምን አገልጋይ ግመሎች ውኃ ስታጠጣ

      ርብቃ ታታሪና እንግዳ ተቀባይ ነበረች

  • “አዎ፣ እሄዳለሁ”
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 3
    • a ርብቃ ውኃ ልትቀዳ የሄደችው አመሻሽ ላይ ነበር። ዘገባው የውኃው ጉድጓድ ጋ ብዙ ሰዓት እንዳሳለፈች ምንም ፍንጭ አይሰጥም። በተጨማሪም ሥራውን ጨርሳ ስትመጣ ቤተሰቦቿ ተኝተው እንደጠበቋት ወይም የተላከችበትን ጉዳይ ለመፈጸም በጣም በመዘግየቷ እሷን ፍለጋ የመጣ ሰው መኖሩን አይጠቁምም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ