-
“አዎ፣ እሄዳለሁ”መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 3
-
-
ርብቃ ለአሥሩ ግመሎች ውኃ ለመስጠት ሐሳብ ያቀረበችው ጠጥተው እስኪረኩ ድረስ እንጂ እንዲቃመሱ ያህል ብቻ አለመሆኑን ልብ በል። ውኃ የጠማው አንድ ግመል ከ95 ሊትር በላይ ውኃ ሊጠጣ ይችላል! አሥሩም ግመሎች በጣም ጠምቷቸው ከነበረ ርብቃ ብዙ ሰዓት የሚፈጅ አድካሚ ሥራ ይጠብቃታል ማለት ነው። የተፈጸመውን ሁኔታ ስናስብ ግመሎቹ በጣም ተጠምተው ነበር ለማለት አያስደፍርም።a ይሁንና ርብቃ ግመሎቹን ለማጠጣት ሐሳብ ስታቀርብ ይህን ታውቅ ነበር? በጭራሽ። ለአካባቢው ባይተዋር ለሆነው ለዚህ አረጋዊ ሰው፣ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ለማሳየት ስትል ጉልበቷን ሳትቆጥብ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኝነቱም ሆነ ጉጉቱ ነበራት። እሱም በሐሳቧ ተስማማ። ከዚያም እንስራዋን ለመሙላት እየተመላለሰች ገንዳው ውስጥ ውኃ ደጋግማ ስትገለብጥ በመገረም ይመለከታት ነበር።—ዘፍጥረት 24:20, 21
ርብቃ ታታሪና እንግዳ ተቀባይ ነበረች
-
-
“አዎ፣ እሄዳለሁ”መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 3
-
-
ርብቃ አረጋዊው ሰው ትክ ብሎ እያያት መሆኑን እንደምታስተውል ግልጽ ነው። እርግጥ እንደዚያ ያያት የነበረው በመጥፎ ዓላማ አይደለም፤ አስተያየቱ መገረሙን፣ መደነቁንና መደሰቱን ይጠቁማል። ርብቃ ሥራውን ስትጨርስ ሰውየው ውድ ጌጣ ጌጦች በስጦታ አበረከተላት! ከዚያም “እስቲ ንገሪኝ፣ ለመሆኑ የማን ልጅ ነሽ? በአባትሽ ቤት የምናድርበት ቦታ ይኖር ይሆን?” ሲል ጠየቃት። ቤተሰቦቿ እነማን እንደሆኑ ስትነግረው ደስታው ወደር አልነበረውም። ርብቃ በደስታ ከመፈንደቋ የተነሳ ሳይሆን አይቀርም “ገለባና ብዙ ገፈራ እንዲሁም ለማደሪያ የሚሆን ስፍራ አለን” በማለት አክላ ተናገረች። ከአረጋዊው ሰው ጋር የሚጓዙ ሌሎች ሰዎችም ስላሉ ይህ ብዙ ወጪ የሚያስወጣ ግብዣ ነው። ከዚያም ያጋጠማትን ነገር ለእናቷ ለመንገር ሰውየውን ጥላው እየሮጠች ሄደች።—ዘፍጥረት 24:22-28, 32
-