-
ሬሳ የማድረቅ ልማድ ለክርስቲያኖች ተገቢ ነውን?መጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 15
-
-
ሬሳ የማድረቅ ልማድ ለክርስቲያኖች ተገቢ ነውን?
ታማኙ ፓትርያርክ ያዕቆብ በሕይወቱ ፍጻሜ ላይ “በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች . . . ዋሻ ናት” የሚል ጥያቄ አቀረበ። —ዘፍጥረት 49:29-31
ዮሴፍ በወቅቱ በግብፅ ውስጥ በሰፊው ይሠራበት የነበረውን ልማድ በመከተል አባቱ የጠየቀውን ፈጽሟል። ዮሴፍ “አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኀኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት” አዘዘ። በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ 50 ውስጥ ተመዝግቦ በሚገኘው ዘገባ መሠረት መድኃኒት ቀማሚዎቹ በተለመደው 40 ቀን ውስጥ ሬሳውን አደረቁ። የያዕቆብ ሬሳ እንዲደርቅ መደረጉ በዝግታ የሚጓዙት እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው የቤተሰቡ አባላትና የግብፅ መኳንንቶች 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘው የያዕቆብን አስከሬን ኬብሮን ለመቅበር አስችሏቸዋል።—ዘፍጥረት 50:1-14 የ1980 ትርጉም
በመድኃኒት እንዲደርቅ የተደረገውን የያዕቆብ አስከሬን አንድ ቀን ማግኘት ይቻል ይሆን? አስከሬኑን የማግኘቱ አጋጣሚ እጅግ የመነመነ ነው። የእስራኤል ምድር ውኃ የሞላበት አካባቢ የነበረ መሆኑ ሰው ሠራሽ ቅርሶችን የማግኘቱን አጋጣሚ ውስን አድርጎታል። (ዘጸአት 3:8) ከብረት ወይም ከድንጋይ የተሠሩ ጥንታዊ ዕቃዎችን በብዛት ማግኘት ቢቻልም እንደ ልብስ፣ ቆዳና የደረቀ አስከሬንን የመሰሉ በቀላሉ ሊበሰብሱ የሚችሉ አብዛኞቹ ነገሮች እርጥበቱንና ተለዋዋጭ የተፈጥሮ ክስተቶችን መቋቋም አይችሉም።
-
-
ሬሳ የማድረቅ ልማድ ለክርስቲያኖች ተገቢ ነውን?መጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 15
-
-
የያዕቆብን አስከሬን በመድኃኒት ያደረቁት ሰዎች ከእርሱ ጋር የሚመሳሰል ሃይማኖታዊ እምነት ያላቸው ሰዎች አልነበሩም። ሆኖም ዮሴፍ የአባቱን አስከሬን ለመድኃኒት ቀማሚዎች ሲሰጥ በወቅቱ ግብፅ ውስጥ ሬሳ በሚደርቅበት ጊዜ ይደረግ የነበረው ዓይነት የጸሎትና ሌላ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እንዲደረግ ጠይቋል ብሎ ማሰቡ ፈጽሞ የማይመስል ነው። ያዕቆብም ሆነ ዮሴፍ የእምነት ሰዎች ነበሩ። (ዕብራውያን 11:21, 22) ምንም እንኳን ይሖዋ የያዕቆብ አስከሬን ሳይፈርስ እንዲቆይ ያዘዘ ባይሆንም በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ድርጊቱ እንደተወገዘ የሚያሳይ ምንም ሐሳብ የለም። የያዕቆብ ሬሳ እንዲደርቅ መደረጉ ለእስራኤል ሕዝብም ሆነ ለክርስቲያን ጉባኤ ምሳሌ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። እንዲያውም በአምላክ ቃል ውስጥ ይህን በሚመለከት የተሰጠ ግልጽ የሆነ መመሪያ የለም። የዮሴፍ አስከሬን እዚያው ግብፅ ውስጥ እንዲደርቅ መደረጉን ከሚገልጸው ታሪክ በኋላ ስለዚህ ድርጊት የሚናገር ሌላ ተጨማሪ ሐሳብ በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ አይገኝም።—ዘፍጥረት 50:26 አ.መ.ት
-