የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከግብፅ ሃብት የሚልቅ ነገር
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • አስተዳደግና ትምህርት

      ዮካብድ “ሕፃኑን ወስዳ አጠባችው። ሕፃኑም አደገ፣ ወደ ፈርዖንም ልጅ ዘንድ አመጣችው፣ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት።” (ዘጸአት 2:​9, 10) መጽሐፍ ቅዱስ ሙሴ ከሥጋ ወላጆቹ ጋር ለምን ያህል ጊዜ እንደኖረ አይገልጽም። አንዳንዶች ቢያንስ ጡት እስኪጥል ማለትም ሁለት ወይም ሦስት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ቆይቶ መሆን አለበት በማለት ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ከዚህ የበለጠ ጊዜም ቆይቶ ሊሆን ይችላል። የዘጸአት መጽሐፍ የሚገልጸው ወላጆቹ ‘እንዳሳደጉት’ ብቻ ነው። ከዚህ አገላለጽ ደግሞ እድሜውን በትክክል መናገር አይቻልም። ያም ሆነ ይህ አንበረምና ዮካብድ ይህንን ጊዜ ሙሴን ስለ ይሖዋ ለማስተማርና ዕብራዊ መሆኑን እንዲያውቅ ለማድረግ እንደተጠቀሙበት ምንም ጥርጥር የለውም። ወላጆቹ በሙሴ ልብ ውስጥ እምነትንና የጽድቅ ፍቅርን በመትከል ረገድ ምን ያህል እንደተሳካላቸው የሚያሳየው ጊዜ ብቻ ይሆናል።

  • ከግብፅ ሃብት የሚልቅ ነገር
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • [በገጽ 11 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

      ከሚያጠቡ ሞግዚቶች ጋር የሚደረግ ውል

      አብዛኛውን ጊዜ እናቶች የገዛ ልጆቻቸውን ያጠባሉ። ሆኖም ምሁሩ ብሬቫርድ ቻይልድስ ጆርናል ኦቭ ቢብሊካል ሊትሬቸር በተባለው ጽሑፋቸው ላይ እንደሚከተለው ብለዋል:- “አንዳንድ የባላባት [በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ] ቤተሰቦች አልፎ አልፎ ጡት አጥቢ ሞግዚት ይቀጥሩ ነበር። በተጨማሪም እናቲቱ ማጥባት ሳትችል ስትቀር ወይም ማንነቷ ሳይታወቅ ሲቀር ሕፃኑን እያጠባች የምታሳድግ ሞግዚት ትቀጠር ነበር። ሞግዚቷ በተሰጣት የጊዜ ገደብ ውስጥ ልጁን የማጥባትና የማሳደግ ኃላፊነት ነበረባት።” እያጠቡ ከሚያሳድጉ ሞግዚቶች ጋር የተደረጉ በርካታ ውሎች የሰፈሩባቸው ጥንታዊ ፓፒረሶች በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ተገኝተዋል። እነዚህ መዛግብቶች ከሱመሪያን ዘመን አንስቶ በግብፅ ሰፍኖ የነበረው የግሪክ ባሕልና አስተሳሰብ እስከከሰመበት ዘመን ድረስ ተስፋፍቶ የነበረውን ልማድ ይጠቁማሉ። መዛግብቱ ከያዟቸው ዋና ዋና ሐሳቦች መካከል ውሉን የተዋዋሉት ሰዎች ያሰፈሯቸው ሐሳቦች፣ ውሉ የሚጸናበት ጊዜ፣ የሥራው ሁኔታ፣ ስለ አመጋገብ የተሰጡ ዝርዝር ሁኔታዎች፣ ውሉን አለማክበር ስለሚያስከትለው ቅጣት፣ ደመወዝና ደመወዙ ስለሚከፈልበት መንገድ የሚገልጹ ሐሳቦች ይገኙበታል። ቻይልድስ አብዛኛውን ጊዜ “ውሉ ለሁለት ወይም ለሦስት ዓመታት ይቆይ” እንደነበረ ገልጸዋል። “ሞግዚቷ ሕፃኑን ቤቷ ወስዳ ታሳድገዋለች። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ የልጁን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል ወደ ባለቤቱ እንድትመልሰው ትጠየቅ ነበር።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ