-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥር 15
-
-
ከግብፅ ከወጡ በኋላ ብዙም ሳይቆይ እስራኤላውያን ምግብን በተመለከተ ማጉረምረም ጀመሩ። በዚህም ምክንያት ይሖዋ መና ሰጣቸው። (ዘፀአት 12:17, 18፤ 16:1-5) በዚያን ወቅት ሙሴ አሮንን እንዲህ ሲል አዘዘው:- “አንድ ማሰሮ ወስደህ አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለሚመጡት ትውልዶች እንዲቆይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው።” ዘገባው በመቀጠል “እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮን፣ መናው ይጠበቅ ዘንድ በምስክሩ ፊት [ጠቃሚ ሰነዶች በአስተማማኝ ሁኔታ የሚቀመጡበት መያዣ ነው] አስቀመጠው” በማለት ይገልጻል። (ዘፀአት 16:33, 34) በዚህ ጊዜ አሮን መና ሰብስቦ በማሰሮ ውስጥ እንዳስቀመጠ ምንም ጥያቄ የለውም። ሆኖም መናው በምስክሩ ፊት እንዲቀመጥ ሙሴ ታቦቱን እስኪሠራና ጽላቶቹን በውስጡ እስኪያደርግ ድረስ መጠበቅ ሳያስፈልግ አይቀርም።
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥር 15
-
-
መናው እስራኤላውያን በ40 ዓመት የምድረ በዳ ቆይታቸው ወቅት አምላክ ያደረገላቸው ዝግጅት ነበር። የተስፋይቱን ‘ምድር ፍሬ በበሉበት ቀን’ መናው መውረዱን አቆመ። (ኢያሱ 5:11, 12) የአሮንም በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ የተቀመጠው በዓላማ ሲሆን ይህም ለምልክትነት እንዲያገለግል ወይም ዓመጸኛ ለሆነው ትውልድ ምሥክር እንዲሆን ነበር። ይህም ቢያንስ በምድረ በዳ ጉዞ ወቅት በትሩ ከዚያ ሳይነሳ መቆየቱን ይጠቁማል። ስለዚህ እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በሌላ በኩል ደግሞ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ከመወሰኑ በፊት የአሮን በትርና መና ያለበት የወርቅ መሶብ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ወጥተዋል ብሎ መደምደም ምክንያታዊ ይመስላል።
-